“በጎበዝ አለቆች”ላይ እርምጃ ተወስዶ ስርአት አልበኝነት ቀንሷል
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በድንገት እንደታወጀ ጦርነት እንደሚያየው ብልጽግና ፓርቲ ገልጿል
ህዝብ ሲያማርሩ በነበሩ “ታጣቂዎች እና የጎበዝ አለቆች”ላይ እርምጃ በመወሰዱ ስርአት አልበኝነት ቀንሷል-የብልጽግና ፓርቲ
ህዝብ ሲያማርሩ በነበሩ “ታጣቂዎች እና የጎበዝ አለቆች”ላይ እርምጃ በመወሰዱ ስርአት አልበኝነት ቀንሷል-የብልጽግና ፓርቲ
የብልጸግና ፓርቲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ“በተለያዩ አካባቢዎች ሕዝቡን እያማረሩ የነበሩ ታጣቂዎች እና የጎበዝ አለቆችን አደብ ለማስገዛት በተወሰደ ርምጃ ሥርዓት አልበኝነትን” መቀነስ መቻሉን አስታውቋል፡፡
ፓርቲው ቫይረሱ በኢትዮጵያ ሊያስከትል የሚችለውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ለመምክር ተሰብስቦ ነበር፡፡
ፓርቲው “ከዴሞክራሲ ሪፎርሙ ጎን ለጎን የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ጠንካራ የሕግ ማስከበር ተግባራት ለፍሬ በቅተው ከሞላ ጎደል ወደ ሰላማችን ተመልሰናል” ብሏል፡፡
“ወረርሽኙን በድንገት እንደታወጀብን ጦርነት በመሆኑ በፍጥነት ጥቃት እያደረሰብን ” ይገኛል ያለው ኢኮኖሚቀውን ለማረጋጋት እንደሚሰራ ገልጿል፡፡
መንግስት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ለአምስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በትናንትናው እለት ማወጁ ይታወሳል፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትናንት በነበረው ስብስባ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየጨመረ በመምጣቱና መንግስት እስካሁን ከወሰዳቸው እርምጃዎች ተጨማሪ ውሳኔዎች በማስፈለጋቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን አስታውቋል፡፡
የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት “ከተለመደው ህገ-መንግስታዊ አሰራር ወጥቶ በልዩ ሁኔታ መንቀሳቀስ” እንደሚያስችል የገለጸው ጠቅላይ አቃቤ ህግ “የመንግስት ሥልጣን ላይ ያሉ ገደቦች ወይም የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች በተለየ ሁኔታ ለጊዜው ተፈጻሚነታቸው ቀርቶ በሙሉ ኃይል፣ በተቀላጠፈ እና በተቀናጀ መልኩ ለወረርሽኙ ምላሽ መስጠት” እንዲቻል አዋጁ ታውጇል ብሏል፡፡
በኢትዮጵያ እስካሁን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሶስት ሰዎች የሞቱ ሲሆኑ በቫይረሱ የተጠቁ ሶች ቁጥር ደግሞ ወደ 65 ከፍ ብሏል፡፡ በቫይረሱ ከተያዙት ሰዎች መካከል እስካሁን 4 ሰዎች አገግመዋል፡፡
የኮሮና ቫይረሰ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ መጋቢት 4፣ 2012 መገኘቱ ከተረጋገጠ በኋላ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተገኝቷል፡፡