ፖላንድ የጀርመን ፓትሪዮት ሚሳይል ባትሪዎችን በግዛቷ ላይ ለመትከል ፈቃደኛ መሆኗን ገለጸች
ፓትሪዮት ሚሳይል ባሊስቲክ ሚሳይሎችንና የጦር አውሮፕላኖችን ለመቋቋም የሚስችል የአየር መከላከያ ዘዴ ነው
ጀርመን በፖላንድ የፓትሪዮት ሚሳኤል ባትሪዎችን ስትተክል ከአሜሪካ ቀጥሎ ሁለተኛ ሀገር መሆኗ ነው
እንደፈረንጆቹ ህዳር 21፣ ጀርመን ፖላንድን በአሜሪካ የተሰሩ የፓትሪዮት ሚሳይል ባትሪዎችን ከዩክሬን ጋር በምትዋሰንበት ምስራቃዊ ድንበር ላይ እንድትተክል ጥያቄ አቅርባላት እንደነበር አይዘነጋም፡፡
በወቅቱ ለጀርመን ምላሽ የሰጠችው ፖላንድ ባትሪዎቹ በግዛቷ ላይ እንዲከተሉ ፈቃደኛ አለመሆኗ ገልጻ ነበር፡፡
ጀርመን ያቀረበችውን ጥያቄ “በዩክሬን ምድር ማድረግ ስትችል እኛን መጠየቅ አይጠበቅባት”ም ነበር ያለችው ፖላንድ በወቅቱ ፡
ይሁን እንጅ አሁን ላይ የፖላንድ መንግስት ከሳምንት በፊት ለጀርመን የሰጠውን ምላሽ በመቀልበስ በርሊን ባትሪዎቹ በፖላንድ ግዛት ላይ ለመትከል እንምትችል ማስታወቁ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የፖላንድ መከላከያ ሚኒስትር ማሪየስ ብላዝዛክ ማክሰኞ እለት ከጀርመን አቻቸው ክሪስቲን ላምብሬክት ጋር መነጋገራቸውን የሃሳብ ለውጥ ማድረጋቸው በትዊተር ገጻቸው ባጋሩት መልእክት ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ "ከጀርመን መከላከያ ሚኒስቴር ሰዎች ጋር ከተነጋገርኩ በኋላ የዩክሬንን ድጋፍ ውድቅ ለማድረግ የተደረገውን ውሳኔ በመቀበሌ ቅር ተሰኝቼ ነበር። ፓትሪዮት ሚሳይሎችን ወደ ምዕራብ ዩክሬን መትክል የፖላንዳውያን እና የዩክሬናውያንን ደህንነት በአንድ ጊዜ የሚያጠናክር ነው"ም ብለዋል፡፡
"ከዚህ በመነሳት በፖላንድ ውስጥ የሚተከሉ ባትሪዎች የት መሆን እንዳለባቸውና ከዋናው የማዘዣ ሲስተም ማዕከላችን ጋር ለማገናኘት ተግባራዊ ውሳኔዎችን እያደረግን ነው" ሲሉም አክለዋል ፡፡
ጀርመን በፖላንድ የፓትሪዮት ሚሳኤል ባትሪዎችን ስትተክል ከአሜሪካ ቀጥሎ ሁለተኛ ሀገር መሆኗ ነው፡፡
የጀርመን ጥያቄ የመጣው በቅርቡ በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ የፖላንድ መንደር ውስጥ በተተኮሱ ሚሳኤሎች ሁለት ሰዎች መሞታቸው ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡
ዋርሶ እና ኔቶ ሚሳይሎቹ የሩስያ የአየር ጥቃትን ለመከላከል በዩክሬን አየር መከላከያ የተተኮሱ ናቸው ቢሎም የተቀረው ዓለም ሞስኮን ያወገዘበት አጋጠሚ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ፓትሪዮት ሚሳኤል ታክቲካል ባሊስቲክ ሚሳኤሎችን፣ ክሩዝ ሚሳኤሎችን እና ዘመናዊ የጦር አውሮፕላኖችን ለመቋቋም የሚስችል ሁሉን አቀፍ የአየር መከላከያ ዘዴ መሆኑ ይታወቃል።