ፖላንድ ጀርመን በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ላደረሰችባት ጉዳይ ካሳ እንድትከፍላት ጠየቀች
ፖላንድ በጀርመን ለደረሰባት ጉዳት 1 ነጥብ 2 ትሪሊዮን ዶላር እንዲከፈላት ጠይቃለች
ጀርመን በበኩሏ የዓለም ጦርነት ካሳ ጉዳይ የተዘጋ አጀንዳ መሆኑን ገልጻለች
ፖላንድ ጀርመን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ላደረሰችባት ጉዳይ ካሳ እንድትከፍላት ጠየቀች።
ፖላንድ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በአዶልፍ ሂትለር የሚመራው የጀርመን ናዚ ጦር ቀድማ የተያዘች ሀገር ነበረች።
እንዲሁም በእነ አሜሪካ የሚመራው ህብረት የጀርመን ናዚ ጦርን ሲያሸንፍም ፖላንድ በድጋሜ የጦር ሜዳ ሆናም ነበር።
የሁለቱ ቡድን ባካሄዱት የጦርነቱ መጀመርያ እና መቋጫ ላይ ብርቱ ክንድ ያረፈባት ፖላንድ የዓለም ጦርነት ቀስቃሿ ጀርመን በመሆኗ ካሳ ልትከፍለኝ ይገባል ስትል ገልጻለች።
ፖላንድ ጀርመን በቆሰቆሰችው ጦርነት 1 ነጥብ 3 ትሪሊዮን ዶላር ኪሳራ ስለደረሰብኝ ካሳ እንዲከፈላት የሀገሪቱ ግዢ ፓርቲን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።
የአውሮፓ ህብረት እና የኔቶ ዋነኛ አጋር የሆነችው ፖላንድ ለጀርመን ይሄንን ጥያቄ ማቅረቧ በአውሮፓ ህብረት ትብብር ላይ እንቅፋት እንዳይፈጥር ተሰግቷል።
ጀርመን በበኩሏ የመጀመሪያውም ሆነ ሁለተኛው የዓለም ጦርነቶች በወቅቱ በተደረጉ ስምምነቶች አማካኝነት ተቋጭቷል ብላለች።
ፖላንድ ከሶስት ዓመት በፊት ጀርመን 850 ቢሊዮን ዶላር እንድትከፍላት ጠይቃ ነበር።
ዩክሬን በሩሲያ መወረሯን ተከትሎ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት ዩክሬንን በመርዳት ላይ ሲሆኑ ጀርመን የሚጠበቅባትን ያህል እያገዘች አይደለም በሚል እየተተቸች ትገኛለች።
ከነዚህ ተቺ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ፖላንድ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ካሳ እንዲከፈላት ለመጠየቋም አንዱ ገፊ ምክንያት እንደሆነ ተጠቅሷል።
የዩክሬን ጎረቤት የሆነችው ፖላንድ አውሮፓውያን ከሩሲያ ነዳጅ መግዛታቸውን እንዲያቆሙ በመወትወት ላይ ስትሆን በዋነኝነት ጀርመን የሩሲያን ነዳጅ መግዛት እንድታቆም በይፋ ጠይቃለች።