በትራምፕ ላይ ለሶስተኛ ጊዜ የተቃጣ የግድያ ሙከራ መክሸፉ ተነገረ
ፖሊሱ እንዳሉት ከሆነ ይህ ግለሰብ ከጠብመንጃ በተጨማሪ የበርካታ ሀገራት ፓስፖርት እና ሀሰተኛ የመኪና ታርጋ በእጁ ተገኝቶበታል
ትራምፕ ባለፈው ቅዳሜ በካሊፎርንያ የምርጫ ቅስቀሳ ባካሄዱበት ወቅት በፍተሻ ኬላ የተቀባበለ ጠብመንጃ ይዞ የተገኘ አንድ ግለሰብ እንዲታሰር መደረጉን ፖሊስ ገልጿል
በትራምፕ ላይ ለሶስተኛ ጊዜ የተቃጣ የግድያ ሙከራ መክሸፉ ተነገረ።
የሪፐብሊካኑ ፕሬዝደንታዊ እጩ ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ቅዳሜ በካሊፎርንያ የምርጫ ቅስቀሳ ባካሄዱበት ወቅት በፍተሻ ኬላ የተቀባበለ ጠብመንጃ ይዞ የተገኘ አንድ ግለሰብ እንዲታሰር መደረጉን ፖሊስ ገልጿል።
ፖሊሱ እንዳሉት ከሆነ ይህ ግለሰብ ከጠብመንጃ በተጨማሪ የበርካታ ሀገራት ፓስፖርት እና ሀሰተኛ የመኪና ታርጋ በእጁ ተገኝቶበታል።
የሪቨርሳይድ ግዛት ፖሊስ ባልደረባ ቻድ ቢያንኮ እንደገለጹት የፖሊስ ክፍሉ ጥርጣሪ ቢሆንም በትራምፕ ላይ የተቃጣን የግድያ ሙከራ አክሽፈናል ብለው እንደማያምኑ ተናግረዋል። ተጠርጣሪው የዋስ መብቱ ተከብሮ ባለፈው ቅዳሜ መለቀቁን ሮይተርስ ዘግቧል።
የፌደራል ባለስልጣን ባለፈው ቅዳሜ እንደተናገሩት ምርመራው በፌደራል ደረጃ እየተካሄ ነው።
"አሁን የምናውቀው ግለሰቡ በተለያዩ ስሞች በርካታ ፖስፖርቶችን፣ ያልተመዘገበ የመኪና ታርጋ እና የተቀባበለ መሳሪያ ይዞ መገኘቱን ነው" ሲሉ ፖሊሱ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። "ሌላኛውን የግድያ ሙከራ አክሽፈናል ብዬ በጽኑ አምናሉሁ።"
ፖሊሱ እንደገለጹት የላስቬጋስ ነዋሪ የሆነው የ49 አመቱ ቬም ሚለር መኪና እያሽከረከረ ባለበት ወቅት ቅዳሜ 10 ሰአት አካባቢ በፖሊስ እንዲቆም ተደርጎ በቁጥጥር ስር ውሏል። በወቅቱ ትራምፕ ወደ መድረክ አልወጡም ነበር።
ሮይተርስ እስር ቤት ማስረጃዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው ሚሊር የተቀባበለ መሳሪያ በመያዝ ክስ ከተመሰረተ በኋላ በ5ሺ ዶላር ዋስ ከእስር ሊለቀቅ ችሏል።
"ክስተቱ የቀድሞውን ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕንም ሆነ ታዳሚዎቹን ለአደጋ ያጋለጠ አልነበረም"ብለዋል ፖሊሱ።
የአሜሪካ አቃቤ ህግ የሎስአንጀለስ ቢሮ ባወጣው መግለጫ የአሜሪካ የሚስጢራዊ ደህንነት አገልግሎትን ጠቅሶ የፕሬዝደንቱ ደህንነት አደጋ ውስጥ አለመውደቁን ገልጿል። መግለጫው አክሎም እስካሁን ተጨማሪ እስሮች አለመኖራቸውን እና ምርመራው እየተካሄደ ነው ብሏል።
ትራምፕ ባለፈው ሐምሌ በፔንስልቬንያ በተካሄደ የምርጫ ቅስቀሳ ጆሯቸውን ተመተው ለጥቂት መትረፋቸው ነበር። ባለፈው መስከረም ወር ደግሞ የአሜሪካ ሚስጢራዊ ደህንነት አገልግሎት በትራምፕ ፓልም ቢች አቅራቢያ መሳሪያ ይዞ ተደብቆ ያገኘውን ግለሰብ በግድያ ሙከራ ጠርጥሮ መክሰሱ ይታወሳል። እነዚህ የግድያ መከራዎች በሚስጢራዊ ደህንነት አገልግሎቱ እቅድ እና ምላሽ ላይ ጥያቄዎችን አስነስተዋል።