የአርቲስት ሀጫሉን ግድያ ተከትሎ ታስረው የነበሩት ኢንጂነር ይልቃል ከሁለት ወር እስር በኋላ ተፈቱ
የአርቲስት ሀጫሉን ግድያ ተከትሎ ታስረው የነበሩት እንጂነር ይልቃል ከሁለት ወር እስር በኋላ ተፈቱ
ሰኔ 25 ቀን 2012 ዓ.ም. ምሽት አራት ሰዓት ላይ በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩት የኢትዮጵያውያን ሃገር አቀፍ ንቅናቄ (ኢሃን) ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት ከእስር መለቀቃቸውን ፓርቲው አስታወቀ፡፡
የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባል ምዕራፍ ይመር ለአል ዐይን እንደገለጹት ኢንጅነር ይልቃል ዛሬ በዋስትና ከእስር ተለቀዋል፡፡
ከሁለት ወራት በላይ በእስር ላይ የቆዩት ፖለቲከኛው ዛሬ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በተለምዶ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተብሎ ከሚጠራው ማረሚያ ቤት በዋስ ተለቀዋል፡፡
ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግዲያ በኋላ በነበረው እስር ከታሰሩት መካከል የሚጠቀሱት ኢንጅነር ይልቃል ከታሰሩ በኋላ ሕገ መንግስቱ በሚፈቀደው አግባብ መሰረት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ መቆየታቸውን መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን ቤተሰቦቻቸው እንዳይጠይቋቸው እንደተከለከሉ ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡