ታመው ሆስፒታል የገቡት የሮማው ጳጳስ ፍራሲስ በሳምባ ምች መጠቃታቸውን ቫቲካን አስታወቀች
ደብል ኒሞኒያ በሁለቱም ሳምባዎች ላይ ቃጠሎና ጠባሳ የሚፈጥርና መተንፈስን አስቸጋሪ የሚያደርግ ነው

ጳጳሱ በወጣነት ዘመናቸው ባጋጠማቸው የሳምባ ምች ምክንያት የተወሰነው የሳምባ ክፍላቸው ተወግዷል
ታመው ሆስፒታል የገቡት የሮማው ጳጳስ ፍራሲስ በሳምባ ምች መጠቃታቸውን ቫቲካን አስታወቀች።
የሮማው ጳጳስ ፍራንሲሲ በተመንፈሻ አካላቸው ላይ ያጋጠማቸውን ህመም ለመታካም ሆስፒታል ከገቡ ስድስተኛ ቀናቸውን ማስቆጠራቸው ቫቲካን የእሳቸውን ሁኔታ አስመልክታ ባወጣችው ወቅታዊ መረጃ አስታውቃለች።
ጳጳሱ ሁለቱም ሳንባቸው በኒሞኒያ ወይም እጥፍ ሳምባ ምች(ደብል ኒሞኒያ) መጠቃት መጀመሩን ያረጋገጠችው ቫቲካን ከአምስት ቀናት በፊት ሮም በሚገኘው ጀመሊ ሆስፒታል የገቡትን የ88ቱን ጳጳስ ህክምና አወሳስቦታል ብላለች።
ደብል ኒሞኒያ በሁለቱም ሳምባዎች ላይ ቃጠሎና ጠባሳ የሚፈጥርና መተንፈስን አስቸጋሪ የሚያደርግ ነው።
ቫቲካን ቀደም ሲል ሁለት ወይም ከእዚያ በላይ ደቂቅ ህዋሳት ሲገናኙ የሚፈጠረው ፖሊማይክሮቢያል ተጠቂ መሆናቸውንና ጤናቸው እስኪመለስ ድረስ ሆስፒታል እንደሚቆዩ ገልጻ ነበር።
ሮይተርስ በጳጳሱ ሁኔታ መረጃ እንዲሰጥ ፍቃድ ባለመኖሩ ምክንያት ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገን የቫቲካን ባለስልጣን ጠቅሶ እንደዘገበው ጳጳሱ ቬንትሌተር እየተጠቀሙ አለመሆናቸውንና በራሳቸው እየተነፈሱ እንደሚገኙ ገልጿል።
ባለስጣኑ እንደገለጹት ሆስፒታል ውስጥ ከአልጋ ላይ ተነስተው በመቀመጥ የተለመደ ስራቸውን እየሰሩ ናቸው። ቫቲካን በጳጳሱ ሁኔታ ዛሬ ምሽት ላይ አዲስ መረጃ ይፋ ታደርጋለች ተብሎ እንደሚጠበቅ ዘገባው ጠቅሷል።
ጳጳሱ በቅርብ አመታት ውስጥ የጤና መቃወስ አጋጥሟቸዋል። ጳጳሱ በወጣነት ዘመናቸው ባጋጠማቸው የሳምባ ምች ምክንያት የተወሰነው የሳምባ ክፍላቸው ተወግዷል።
አሁን ላይ ጳጳጱ ከህዝብ ፊት የሚቀርቡባቸው እስከ ቅዳሜ ያሉት መርሃግሮች የተሰረዙ ሲሆን በታተመው የቫቲካን ቀን መቁጠሪያ መሰረት ይፋዊ መርሃግብር የላቸውም።