ፖፕ ፍራንሲስ አሁኑኑ እንዲሞቱ የጸለዩ ቄሶች ይቅርታ ጠየቁ
ቄሶቹ ፖፕ ፍራንሲስ ወደ ገነት እንዲሄዱ በቡድን ሲጸልዩ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል ለብዙዎች ተዳርሷል
በመጨረሻም እነዚህ ቄሶች ይቅርታ መጠየቃቸው ተገልጿል
ፖፕ ፍራንሲስ አሁኑኑ እንዲሞቱ የጸለዩ ቄሶች ይቅርታ ጠየቁ፡፡
በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቄሶች ናቸው የተባሉ ቄሶች በቡድን ፖፕ ፍራንሲስ እንዲሞቱ ሲጸልዩ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል ብዙ ተመልካች አግኝቷል፡፡
ብዙዎች የቄሶቹን ድርጊት ኮንነው አስተያየት የሰጡ ሲሆን ብዙዎች ደግሞ ጉዳዩን በመዝናኛነት እንደተመለከቱት አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
በስፓኒሽ ቋንቋ ጸልየዋል የተባሉት እነዚህ ቄሶች ጸሎታቸው በበይነ መረብ ቀጥታ እየተላለፈ ነበር የተባለ ሲሆን አንድ ቄስ “አሁን ደሞ ፖፕ ፍራንሲስ አሁኑኑ ወደ ገነት እንዲሄዱ እጸልያለሁ” ሲሉ አብረው የነበሩ ሁሉም ቄሶች ሲስቁ ታይተዋል ሲል ኤፒ ዘግቧል፡፡
ፖፕ ፍራንሲስ በአየር ንብረት ለተጎዱ ደሃ ሀገራት የእዳ ስረዛ እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ
ሌላኛው ቄስም ለፖፕ ፍራንሲስ የሚደረገውን ጸሎት እንደሚደግፍ አስተያየት ሲሰጥ ቀሪዎቹ ቄሶች ቡቡድን እንደሳቁም ተገልጿል፡፡
በፖፕ ፍራንሲስ ላይ ሲዘባበቱ ነበሩ የተባሉት ስድስት ቄሶችም ባደረጉት ነገር መጸጸታቸውን ገልጸው ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡
ከስድስት ሀገራት የተውጣጡ ናቸው የተባሉት እነዚህ ቄሶች ያደረጉት ነገር ወግ አጥባቂ የሆኑ ፖለቲከኞች ጉዳዩን የፖለቲካ አጀንዳ አድርገውታልም ተብሏል፡፡
ቄሶቹ ያገለግሉበት የነበረው ቤተ ክርስቲያን ጉዳዩን አውግዞ ድርጊቱን የኮነነ ሲሆን ቤተ ክርስቲያናችንን የሚከፋፍል እንዲህ አይነት ነገር ተቀባይነት የለውም ሲል አስታውቋል፡፡
ቤተ ክርስቲያኗም የቄሶቹ ድርጊት ቤተ ክርስቲያኗን እንደማይወክል መሰል ድርጊቶችም በሀይማኖታችን ላይ መከፋፈል እንዲመጣ በር የሚከፍት በመሆኑ የሚወገዝ ነው ስትል መግለጫ ማውጣቷ ተገልጿል፡፡