የአረብ ኤሚሬትስና የቱርክ የውጭ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮቹ በቀጠናዊ ጉዳዮችና በኃይል ዘፍር ተወያዩ
የአረብ ኤሚሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አብዱላህ ቢን ዛይድ ከቱርክ አቻቸው ሜቭሉት ካቩሶግሉ ጋር በአቡዳቢ ተወያይተዋል
አረብ ኤሚሬትስና ቱርክ በቢሊዮኖች ዶላር የሚቆጠር የመዋዕለ ነዋይ ስምምነቶችን መፈራረማቸው ይታወሳል
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ ከቱርክ አቻቸው ሜቭሉት ካቩሶግሉ ጋር በቀጠናዊ ጉዳዮች ተወያዩ
የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮቹ በቀጠናዊ ጉዳዮችና በኃይል ዙሪ መምከራቸው ተነግሯል።
ባለፈው ዓመት ቱርክ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የኃይል ስምምነቶችን ጨምሮ በቢሊዮኖች ዶላር የሚቆጠር የመዋዕለ ነዋይ ስምምነቶችን መፈራረማቸው ይታወሳል።
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ እና የቱርክ አቻቸው ሜቭሉት ካቩሶግሉ በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ተወያይተዋል።
ውይይቱ ከሲር ባኒያስ ፎረም ጎን ለጎን መሆኑን የጠቀሰው የኤሚሬትስ የዜና አገልግሎት፤ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭም ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ሼክ አብዱላሂ ካቩሶግሉን በጥቁር ባህር በኩል እህል ወደ ውጭ የመላክ ስምምነት በድጋሚ በመጀመሩ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ይህን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ በቱርክ ሪፐብሊክ በኩል የተደረገውን ከፍተኛ ጥረትም አድንቀዋል።
የአረብ ኤሚሬቶች ዲፕሎማት ሀገራቸው በቱርክ መዋዕለ ነዋይ ለማፍሰስ ፍላጎት እንዳላትም አረጋግጠዋል ተብሏል።
ባለፈው ዓመት ቱርክ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የኃይል ስምምነቶችን ጨምሮ በቢሊዮኖች ዶላር የሚቆጠር የመዋዕለ ነዋይ ስምምነቶችን መፈራረማቸው ይታወሳል።
ይህ ስምምነት የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ከተነጋገሩ በኋላ የተደረሰ ነው።