ድርጊቱ እንዳይቀጥል የተወሰነው የታሰበውን ለውጥ ማምጣት ባለመቻሉ ነው
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የጥቁሮች ህይወት ያገባኛል በሚል የጀመረውን ድጋፍ እንዲቆም ወሰነ።
በአሜሪካ በሚኒያፖሊስ ግዛት ጆርጅ ፍሎይድ የተሰኘው ግለሰብ ፖሊስ አንገቱ ላይ ቆሞ ህይወቱ እንዲያልፍ መደረጉን ተከትሎ ነበር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ጨዋታ ከመጀመራቸው በፊት ድርጊቱን ለማውገዝ በጉልበታቸው እንዲንበረከኩ እና ብላክ ላይቭስ ማተር ወይም የጥቁሮች ህይወት ያገባኛል መልዕክት እንዲተላለፍ የተወሰነው።
ከቀናት በኋላ በሚጀምረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ላይ እንደማይደገም የጨዋታው ባለቤት የእንግሊዝ እግር ኳስ አወዳዳሪ አካል ይህ ድርጊት እንደማይቀጥል ወስኗል።
ተቋም ድርጊቱ እንዳይቀጥል የወሰነው የተጫዋቾች መንበርከክ የታሰበውን በጥቁሮች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ማስቆም ማምጣት ባለመቻሉ እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል።
የክሪስታል ፓላሱ ቦቲዲቯራዊው የመስመር ተጫዋች በተጠናቀቀው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ ከየካቲት ጀምሮ በጉልበቱ መንበርከክ ያቆመ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ አሁንም የዘረኝነት ጥቃቱ ከደጋፊዎች እየደረሰብኝ ነው በሚል ነበር።
የቀድሞው የአሜሪካ ፖሊስ ደርክ ሾቪን በጥቁር አሜሪካዊው ጆርድ ፍሎይድ አንገት ላይ በመቆም ትንፋሽ አጥሮት እንዲሞት ማድረጉ ይታወሳል።
የ45 ዓመቱ የሚያናፖሊስ ፖሊስ ባልደረባ ደርክ ሾቪን በ46 ዓመቱ ጆርድ ፍሎይድ አንገት ላይ ለ9 ደቂቃ አንገቱ ላይ ከቆመበት በኋላ ነበር ሀይወቱ ያለፈው።
ጆርድ ፍሎይድን የገደለው ፖሊስ ደርክ ሾቪን የ22 ዓመት ከ6 ወር እስር ተፈርዶበታል።