በፕሪሚየር ሊጉ በጥር ወር የተደረጉ ዝውውሮች
በፈረንጆቹ ጥር 1 2023 የተጀመረው የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች የተጫዋቾች ዝውውር ከጥቂት ስአታት በኋላ ይጠናቀቃል
የሊጉ መሪ አርሰናልን ጨምሮ አብዛኞቹ የሊጉ ክለቦች በዝውውሩ ተሳትፈዋል
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የጥር ወር የተጫዋቾች ዝውውር ዛሬ የሚጠናቀቅ በመሆኑ ክለቦች በቀሪዎቹ ስአታት ተጫዋቾችን ለማስፈረም እየተሯሯጡ ነው።
ሊጉን ከሚመራው አርሰናል በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ እስከሚገኘው ሳውዛምፕተን ድረስ በፈረንጆቹ ጥር 1 2023 በተጀመረው ዝውውር አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርመዋል፤ ለሌሎች ክለቦችም በውሰት ሰጥተዋል።
የስካይ ኒውስ ዘገባ እንደሚያሳየው ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ኤቨርተን፣ ክሪስታን ፓላስ እና ፉልሃም ብቻ ናቸው አዲስ ተጫዋች ያላስፈረሙት።
በሊጉ 10ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ቼልሲ በጥር ወር የዝውውር ጊዜ ሰባት ተጫዋቾችን በማስፈረም እየመራ ነው።
በሊጉ ዋና ዋና ክለቦች ያስፈረሟቸውን እና በውሰት የሰጧቸውን ተጫዋቾች እንመልከት፦
አርሰናል
የተቀላቀሉ
ሊዮናርዶ ትሮሳርድ - ከብራይተን በ27 ሚሊየን ፓውንድ
ጃኩብ ኪዊየር - ከስፔዚያ በ20 ሚሊየን ፓውንድ
የለቀቁ
ብሮክ ኖርተን ኩፊ - ለእንግሊዙ ኮቨንትሪ (በውሰት)
ሚጉየል አዚዝ - ዊጋን (በውሰት)
ሃሪ ክላርክ - ሊፕዚሽ (በይፋ አልተገለጸም)
ማርኪዩንሆስ - ኖርዊች (በውሰት)
ኦማር ሬኪክ - ዊጋን (በውሰት)
ማንቸስተር ሲቲ
የተቀላቀለ
ማክሲሞ ፔሮን - ከአርጀንቲናው ቬሌዝ ሳርስፊልድ በ8 ሚሊየን ፓውንድ
የለቀቁ
ካንሴሎ - ለባየርሙኒክ (በውሰት)
ሞርጋን ሮጀርስ - ለብላክፑል (በውሰት)
ሊያም ዴላፕ - ለፕሪስተን (በውሰት)
ጆሽ ዊልሰን ኢስብራንድ - ለኮቨንትሪ (በውሰት)
ካይኪ ዳ ሲልቫ ቻጋስ - ለብራዚሉ ባሂያ (በውሰት)
ማንቸስተር ዩናይትድ
የተቀላቀሉ
ጃክ በትላንድ - ከክሪስታል ፓላስ (በውሰት)
ቫውት ቬግሆርስት - ከበርንሌይ (በውሰት)
የለቀቁ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ - ለአል ናስር (በነጻ)
ሾላ ሾርታየር - ለቦልተን (በውሰት)
ቻርሊ ሳቬጅ - ለእንግሊዙ ፎረስት ግሪን (በውሰት)
ቻርሊ ማክኔል - ለዌልሱ ኒውፖርት (በውሰት)
ሊቨርፑል
የተቀላቀለ
ኮዲ ጋክፖ - ከፒ ኤስ ቪ አይንዶቨን በ45 ሚሊየን ፓውንድ
የለቀቁ
ጃክ ኪን - ለእንግሊዙ ስዊንደን ክለብ (የዝውውሩ አይነት አልተገለጸም)
ጃሬል ኩዋንሳህ - ለብሪስቶል ሮቨርስ (በውሰት)
ቼልሲ
የተቀላቀሉ
ሚካሄሎ ሙድሪክ - ከሻካታር ዶኔስክ በ83 ነጥብ 5 ሚሊየን ፓውንድ
ቤኖይት ባዲያሺሌ - ከሞናኮ በ35 ሚሊየን ፓውንድ
ጃኦ ፌሊክስ - ከአትሌቲኮ ማድሪድ በውሰት
ዳቪድ ፎፋና - ከኖርዌዩ ሞልዴ ክለብ (የዝውውር ገንዘቡ አልተገለጸም)
ኖኒ ማዱኬ - ከፓሪስ ሴንት ጀርሜን በ29 ሚሊየን ዶላር
አንድሪ ሳንቶስ - ከብራዚሉ ቫስኮ ደ ጋማ ክለብ (የዝውውር ገንዘቡ አልተገለጸም)
ማሎ ጉስቶ - ከሊዮን በ26 ነጥብ 3 ሚሊየን ፓውንድ
የለቀቁ
ቴዲ ሻርማንሎ - ለእንግሊዙ ሃቫንት ዋተርሎቪል ክለብ (በውሰት)
ጁድ ሰንሱፕ ቤል - ለቶተንሃም (የዝውውሩ አይነት አልተገለጸም)
ቶተንሃም
የተቀላቀለ
አርናውት ዳንጁማ - ከቪያሪያል (በወሰት)
ጁድ ሰንሱፕ ቤል - ከቼልሲ (የዝውውሩ አይነት አልተገለጸም)
የለቀቀ
ብራይን ጊል - ለሲቪያ (በውሰት)