ፕሬዝዳንት ባይደን “ነጭ ብሆንም ደደብ አይደለሁም” ማለታቸውን ተከትሎ ትችቶችን እያስተናገዱ ነው
የፕሬዝዳንቱ የአፍ ወለምታ በቀጣይ በሚያደርጉት ፕሬዝዳናታዊ ምርጫ ላይ ዋጋ ያስከፍላቸዋል ተብሏል
የፕሬዝዳንቱ ተደጋጋሚ ያልተገባ ንግግር ከእድሜያቸው መግፋት ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል እየተባሉ ይገኛሉ
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን “ነጭ ብሆንም ደደብ አይደለሁም” ማለታቸውን ተከትሎ ትችቶችን እያስተናገዱ ነው፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በአደባባይ መድረኮች ላይ የሚያደርጓቸው ንግግሮች እና ድርጊቶች የብዙሃን መገናኛዎች መነጋጋሪያ አጀንዳዎች እየሆኑ ነው፡፡
- ትራምፕ፥ የባይደን አስተዳደር በዩክሬን ምድር 3ኛውን የአለም ጦርነት ሊያስጀምር ነው ሲሉ ወቀሱ
- ሩሲያ የፕሬዝዳንት ባይደንን የዩክሬን ጉብኝት “ቴአትር” ነው ስትል አጣጣለች
ከሰሞኑ ደግሞ በአንድ መድረክ ላይ ተገኝተው “ነጭ ብሆንም ደደብ አይደለሁም” ማለታቸውን የሚያሳይ ቪዲዮ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ በመንሸራሸር ላይ ይገኛል፡፡
በርካታ አሜሪካዊያን በፕሬዝዳንት ባይደን ንግግር ላይ ተቃውሟቸውን ያሰሙ ሲሆን የፕሬዝዳንቱ ንግግር የዘረኝነት ጥቃት ነው ተብሏል፡፡
Biden in a new "racist slip": I'm white, but I'm not stupid
የ80 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ታሪክ አዛውንቱ መሪ ያሰኛቸው ሲሆን ተጨማሪ አራት ዓመታትን በስልጣን ላይ ከቆዩ ደግሞ በራሳቸው የተያዘውን እድሜ ያሻሽሉታል፡፡
የሪፐብሊካን ፖለቲከኞች ፕሬዝዳንቱ እድሜያቸው በመግፋቱ የሚያደርጉትን ነገር እንዳያውቁ ማድረጉን ለተጨማሪ ጊዜም በስልጣን ላይ ሊቆዩ እንደማይገባም በመናገር ላይ ናቸው፡፡
ፕሬዝዳንት ባይደን ከሰባት ዓመት በፊት የባራክ ኦባማ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ቅስቀሳ ላይ "ኦባማ የመጀመሪያ ደረጃ ጥቁር አሜሪካዊ ነው፣ ንጹህ እና ጥሩ የማሰብ አቅም ያለው ነው" ማለታቸውን ተከትሎ ትችቶችን አስተናግደውም ነበር፡፡
እንዲሁም ባይደን ወደ ፕሬዝዳንትነት ከመምጣታቸው በፊትም " ድሃ ህጻናት እንደ ነጭ ህጻናት ባለ ተሰጥኦ ናቸው" በሚል መናገራቸውን ተከትሎ ተመሳሳይ የዘረኝነት ጥቃት አድርሰዋል በሚል ተተችተዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በተደጋጋሚ የሚያደርጓቸው የአፍ ወለምታዎች ዲሞክራት ፓርቲን እና ደጋፊዎቻቸውን ከማስቆጣቱ ባለፈ በቀጣይ ሊያደርጉት ስላሰቡት ፕሬዝዳናታዊ ውድድር ላይ ችግር ሊፈጥርባቸው ይችላል ተብሏል፡፡
የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በፈረንጆቹ 2024 ይካሄዳል የተባለ ሲሆን የምርጫ ቅስቀሳው ከወዲሁ ሲጀመር የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በተመድ የዋሸንግተን አምባሳደር የነበሩት ኒኪ ሀሌይ ዋነኛ ተፎካካሪ እንደሚሆኑ ተገምቷል፡፡የፕሬዝዳንቱ ተደጋጋሚ ያልተገባ ንግግር ከእድሜያቸው መግፋት ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል እየተባሉ ይገኛሉ