ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፤ ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን ለመወዳደር ገና አልወሰንኩም አሉ
ባይደን “በድጋሜ የመመረጥ ዓላማ ቢኖረኝም አሁን ላይ ለመወሰን ጊዜው ገና ነው” ብለዋል
አብዛኞቹ ዴሞክራቶች በ2024 ምርጫ ከጆ ባይደን ይልቅ ሌላ ሰው እንዲወዳደር ይፈልጋሉ መባሉ ይታወሳል
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፤ ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን ለመወዳደር ገና አልወሰንኩም ማለታቸው ተሰምቷል።
የ80 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ከሲቢኤስ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት “በድጋሜ የመመረጥ ዓላማ ቢኖረኝም አሁን ላይ ለመወሰን ጊዜው ገና ነው” ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ባይደን ይህን ይበሉ እንጅ፤ ዋይት ሀውስ ጆ- ባይደን በ2024ቱ ምርጫ እንደገና እንደሚወዳደሩ ደጋግሞ ሲገልጽ መቆየቱ የሚታወስ ነው።
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከሁለት ዓመት በኋላ በሚካሄደው ምርጫ እንደሚሳተፉ የቅርብ ረዳቶቻቸው በወቅቱ ገልጸው ነበር።
የጆ ባይደን ወዳጅና የቀድሞ ሴናተር ክሪስ ዶድ ፕሬዝዳንቱ በአውሮፓውያኑ 2024 በሚደረገው ምርጫ እንደሚወዳደሩ እንደነገሯው ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል ከአሜሪካው ዴሞክራት ፓርቲ አባላት ውስጥ አብዛኞቹ ጆ ባይደን በ2024 ፐሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ በሌላ ሰው እንዲተኩ ፍላጎት ማሳየታቸው ይታወሰሳል።
በዚህም 64 በመቶ የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባላት ለ2024 የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከባይደን ይልቅ ሌላ እጩ መቅረብ እንዳለበት ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።
ከእነዚህም ውስጥ 33 በመቶው የፕሬዝዳንቱን እድሜ በምንያትነት ያስቀመጡ ሲሆን፤ 32 በመቶው ደገሞ የፕሬዝዳንቱን የስራ አፈጻጸም ደካማነትን በምክንያትነት ጠቅሰዋል።
በዴሞክራቲክ ፓርቲ አባላት ላይ በተደረገ ድምጽ የማሰባሰብ ሂደት 26 በመቶ ብቻ ጆ ባይደን በ2024 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በእጩነት እንዲቀርቡ ፍላጎት አለሳይተዋል።