የጣሊያን የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር፤ “ፑቲን ወደ ጦርነት የገባው በፓርቲውና በሚኒስትሮቹ ተገፋፍቶ ነው” አሉ
የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዮ ቤርሎስኮኒ የፕሬዝዳንት ፑቲን የቅርብ ወዳጅ መሆናቸው ይታወቃል
ቤርሎስኮኒ፤ የሩስያ እቅድ ኪቭን "በሳምንት ውስጥ" በመቆጠጠር ዘሌንስኪን ተክቶ መውጣትእንደነበር ተናግረዋል
የቀድሞ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዮ ቤርሎስኮኒ ፕሬዝዳንት ፑቲን በኪቭ አዲስ መንግስት ለመመስረት ከዩክሬን ጋር ጦርነት የገባው “በፓርቲውና በሚኒስትሮቹ ተገፋፍቶ ነው” አሉ።
ቤርሎስኮኒ ፤ የሩሲያ ኃይሎች በዩክሬን ጦር ሜዳ ያጋጠማቸውን ውድቀት ተከትሎ ፑቲን ለሩሲያውያን ያቀረቡት የክተት ጥሪና አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ኒውክሌር እንደሚጠቀም ለመስፈራራት የሄደበት መንገድ ከጅምሩም ቢሆን ፍላጎት እንዳልነበረው የሚያሳይ ነው በማለት የፑቲንን የጦርነት ውስጣዊ ስሜት ዝቅ አድርገውታል።
"ፑቲን በሩሲያ ህዝብ፣ ፓርቲያቸው እና ሚኒስትሮቹ ይህን ልዩ ተግባር እንዲፈጽሙ ተገዶ ነበር" ነው ያሉት ቤርሎስኮኒ፡፡
የሩስያ እቅድ በመጀመሪያ ኪቭን "በሳምንት ውስጥ" በመቆጠጠር የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪን "በጨዋ መንግስት" በመተካት "በሚቀጥለው ሳምንት" መውጣት ነበር ያሉት ቤርሎስኮኒ፤ አሁን እየሆነ ያለው ነገር እንዳልገባቸውም ተናግረዋል፡፡
“በአእምሮዬ የሩሲያ ኃይሎች በኪቭ ዙሪያ መቆየት ሲገባቸው በዩክሬን ለምን እንደተስፋፋ እንኳ ሳስስብ ምንም አልገባኝም ”ብለዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የፑቲን የቅርብ ወዳጅ እንደሆኑ የሚነገርላቸው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዮ ቤርሎስኮኒ አስተያያት ፤ጣሊያን ለምርጫ ሽርጉድ እያለች ባለችበት ዋዜማ የተሰጠ በመሆኑ በምዕራባውያን በኩል ድንጋጤ ሳይፈጥር እንዳልቀረ እየተነገረ ነው።
ድንጋጤው የተፈጠረው ቤርሎስኮኒ እሁድ በሚካሄደው ምርጫ ያሸንፋል ተብሎ የሚጠበቀውን የቀኝ ዘመሞች ጥምረት አንድ አካል የሆነውን የፎርዛ ኢታሊያ ፓርቲ አባል ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ እንደሆነም ነው የሮይተርስ ዘገባ የሚያመለክተው።
እናም የቤርሎስኮኒ አስተያየት የቀኝ ዘመመቹ ጥምረት በዩክሬን ጦርነቱ ላይ ያለው አቋም የሚበትን እንዳይሆን ተሰግቷል፡፡
ጣሊያን በቅርቡ ከስልጣን በተሰናበቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ድራጊ የስልጣን ዘመን ፤ ሞስኮ በኪቭ ላይ የጀመረቸውን ወታደራዊ ዘመቻ ስትቀወምና በምዕራቡ ዓለም በሩሲያ ላይ የተጣሉትን በርካታ ማዕቀቦች ስትደግፍ መቆየቷ አይዘነጋም፡፡