ፖለቲካ
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን ለመወዳደር ማቀዳቸውን ተናገሩ
ባይደን በዲሞክራቲክ ፓርቲያቸው እስካሁን "አስፈሪ ተቀናቃኝ" የላቸውም ተብሏል
በ80 ዓመታቸው ጆ ባይደን በአሜሪካ ታሪክ አንጋፋው ፕሬዝዳንት ናቸው
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በ2024 ምርጫ በድጋሚ መመረጥ እንደሚፈልጉ ፍንጭ ሰጥተዋል።
ባይደን ሰኞ እለት እንደገና ለመወዳደር ማቀዳቸውን ተናግረው ነገር ግን "እስካሁን ይፋ ለማድረግ ዝግጁ አይደለሁም" ብለዋል።
ሩሲያ የፕሬዝዳንት ባይደንን የዩክሬን ጉብኝት “ቴአትር” ነው ስትል አጣጣለች
ፕሬዝዳንት ባይደን ከዚህ ቀደም ለተጨማሪ አራት ዓመታት ለመወዳደር “ፍላጎት” እንዳላቸው ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ ባለፈው ህዳር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሌላ የስልጣን ዘመን ለመፈለግ ያላቸውን ፍላጎት ተናግረው፤ ነገር ግን በዓመቱ መጨረሻ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንደሚማከሩ ተናግረዋል ነበር።
አሁኑ ላይ ለ2024 ምርጫ ከዲሞክራቲክ ወገን ሁለት እጩዎች ቀርበዋል።
በፓርቲያቸው ውስጥ "አስፈሪ ተቀናቃኝ" አለመኖሩ ባይደን ምንም አይነት ጫና ሳይኖርባቸው እጩነታቸውን ለማወጅ ጊዜ ሰጥቷቸዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
በ80 ዓመታቸው ጆ ባይደን በአሜሪካ ታሪክ አንጋፋው ፕሬዝዳንት ናቸው።
በድጋሚ ምርጫ ካሸነፉ በሁለተኛው የስልጣን ዘመናቸው መጨረሻ 86 ዓመታቸውን ይደፍናሉ።