ፕሬዝዳንት ባይደን ስልጣን ከማስረከባቸው በፊት ዩክሬንን ማጠንከር ይፈልጋሉ ተባለ
የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት በሰላም መጠናቀቁ አይቀሬ ቢሆንም በድርድሩ ላይ ዩክሬን የበለጠ ጉልበት እንዲኖራት ፕሬዝዳንቱ ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል
ዩክሬን ከጥር በኋላ በቂ ድጋፍ ስለ ማግኘቷ እርግጠኛ መሆን እንደማይቻል ተገልጿል
ፕሬዝዳንት ባይደን ስልጣን ከማስረከባቸው በፊት ዩክሬንን ማጠንከር ይፈልጋሉ ተባለ፡፡
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ስልጣናቸው ከማብቃቱ በፊት ዩክሬንን የበለጠ ማጠንከር እንደሚፈልጉ ተገልጿል፡፡
የፕሬዝዳንት ባይደን የደህንነት አማካሪ ጃክ ሱልቪያን ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ጋር መክረዋል፡፡
አማካሪው በዚህ ጊዜ እንዳሉት ፕሬዝዳንት ባይደን የስልጣን ቆይታቸው የፊታችን ጥር ወር ላይ የሚያበቃ ሲሆን ከዚያ በፊት ግን ዩክሬን የሩሲያን ጥቃት መመከት የሚያስችላት ድጋፍ ያደርጋሉ ተብሏል፡፡
አሜሪካ ከሁለት ወር በኋላ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለመካሄድ ቀን የቆረጠች ሲሆን በተለይም የሪፐብሊካኑ እጩ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምርጫውን ካሸነፉ ለዩክሬን የሚደረገው ድጋፍ የመቆም እድሉ ሰፊ ነው፡፡
ይህንን ተከትሎ ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጦርነቱን እንዲቆም የመወሰን ስልጣን ያላት ዩክሬን መሆኗን ተናግረዋል የተባለ ሲሆን ከሩሲያ ጋር በሚደረገው ድርድር ላይ የተሻለ አቋም እንዲኖራት ተጨማሪ ድጋፍ ለዩክሬን ማድረግ እንደሚፈልጉ ተገልጿል፡፡
ምዕራባውያን ዩክሬን የረጅም ርቀት ሚሳይሎችን እንድትጠቀም ከፈቀዱ በቀጥታ ከሩሲያ ጋር እንደሚዋጉ ፑቲን አስጠነቀቁ
በያዝነው ወር መጨረሻ ላይ ፕሬዝዳንት ባይደን ለዩክሬን አቻቸው ቮሎዶሚር ዘለንስኪ በነጩ ቤተ መንግስታቸው ግብዣ እንደሚያደርጉላቸው ይጠበቃል፡፡
ዩክሬን ሩሲያ የምታደርስባትን የአየር ለይ ጥቃቶች ለመመከት የረጅም ርቀት ሚሳኤሎችን መጠቀም እንድትችል አሜሪካንን ጨምሮ ምዕራባዊያን ሀገራት እንዲፈቅዱላት እየጠየቀች ትገኛለች፡፡
ፕሬዝዳንት ፑቲን በበኩላቸው የኔቶ ሀገራት ዩክሬን በረጅም ሚሳኤሎች ሩሲያን እንድታጠቃ ከፈቀዱ የቀጥታ ጦርነት ከኔቶ ጋ ሊጀመር እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡