ግሎባል ፋየርፓወር የዩክሬን ወታደራዊ ጥንካሬ ከ145 ሀገራት 18ኛ ደረጃ ላይ የሚያስቀምጣት ነው ብሏል
በወታደራዊ አቅም ዩክሬንን በበርካታ መመዘኛዎች በብዙ እጥፍ የምትበልጠው ሩሲያ የኬቭን 18 በመቶ ይዞታ ተቆጣጥራለች።
ዩክሬንም ከእንድ ወር በፊት በሩሲያዋ ኩርስክ ክልል ድንበር ጥሳ በመግባት ከ130 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ይዣለሁ ብላለች።
ከሁለት አመት በላይ ያስቆጠረው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ተዋናዮቹን እያበዛ የሞስኮና ኬቭን ወታደራዊ አቅም እያዳከመ ቀጥሏል።
የሀገራትን ወታደራዊ ጥንካሬ ደረጃ የሚያወጣው ግሎባል ፋየር ፓወር ሩሲያ በ2024 አሜሪካን በመከተል ሁለተኛዋ ጠንካራ ጦር ያላት ሀገር ናት ብሏል።
ዩክሬንም ከ145 ሀገራት 18ኛ ደረጃን በመያዝ ጠንካራ ወታደራዊ አቅም ካላቸው 20 ሀገራት ውስጥ መካተት ችላለች።
ግሎባል ፋየርፓወር ሩሲያ በአብዛኛው መመዘኛ ዩክሬንን በብዙ እጥፍ እንደምትበልጥ ያነሳል። ለአብነትም የሩሲያ ጦር 4 ሺህ 255 የጦር አውሮፕላኖችን ሲታጠቅ ዩክሬን ያሏት አውሮፕላኖች 321 ብቻ ናቸው።
በርካታ የኒዩክሌር አረር ባለቤት በመሆን ቀዳሚዋ ሞስኮ ከኬቭ በስምንት እጥፍ የሚበልጡ ታንኮች ባለቤት ናት።
ምዕራባውያንም የኬቭን የጦር አውሮፕላን፣ ታንክ እና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ክፍተት ለመሙላት ርብርብ እያደረጉ ቢሆንም በአጭር ጊዜ ከሞስኮ ጋር ያስተካክላታል ተብሎ አይጠበቅም።
የሩሲያ እና ዩክሬን ወታደራዊ አቅም ንጽጽርን በቀጣዩ ምስል ይመልከቱ፦