በመካከላቸው ያለው ወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውጥረት ባየለበት ወቅት፣ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እና የቻይናው አቻቸው ሺ ጅንፒንግ ተገናኝተዋል
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እና የቻይናው አቻቸው ሺ ጅንፒንግ ተገናኙ።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እና የቻይናው አቻቸው ሺ ጅንፒንግ የተገናኙት በመካከላቸው ያለው ወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውጥረት ባየለበት ወቅት መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
መሪዎቹ በአንድ አመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መገናኘታቸው፣ ሁለቱ ተቀናቃኝ ኃያላን በወታደራዊ፣ በእጽ ዝውውር እና በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ውጥረት ያርግበዋል ተብሏል።
ነገርግን በሁለቱ ኃያል መካከል ያለውን ሰፊ ልዩነት ለማጥበብ ሌላ ጊዜ ሊያስፈልጋቸው እንደሚችል ተገልጿል።
ባይደን እና ሺ ለረጅም ጊዜ ባልተግባቡባቸው በታይዋን፣በደቡባዊ የቻይና ባህር፣ በሀማስ እና እስራኤል ጦርነት፣ በዩክሬን ጦርነት እና በሰሜን ኮሪያ እና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ ስለሚወያዩ በሁለቱም ፖሲፊክ በኩል ያሉ ባለስልጣናት ዝቅተኛ ግምት ሰጥተውታል።
በእሲያ-ፖሲፊክ ትብብር(ኤፒኢሲ) ስብሰባ የተገናኙት ባይደን እና ሺ በአሜሪካ ሳንፍራንሲስኮ የደረሱት በትናንትናው እለት ነበር።
21 አባላት ካሉት በድን መሪዎች እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ዋና ስራ አስፈጻሚዎች በሳንፍራንሲስኮ ይገናኛሉ። ይህ ውይይት የሚደረገው ቻይና ኢኮኖሚዋ በተንገራገጨበት እና ከጎረቤት ሀገራት ጋር በድንበር ጉዳይ ውዝግብ ውስጥ በገባችበት ወቅት ነው።
የኢኮኖሚ ጉዳዮች የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ከሚነጋገሩባቸው ጉዳዮች ቀዳሚ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገሞቷል።
የታይዋን ጉዳይም በመሳሳይ መሪዎቹን የሚያነጋግር አጀንዳ ይሆናል ተብሏል።
አሜሪካ ከታይዋን ጋር ወታደራዊ ግንኙት ለመፍጠር በተለያየ ጊዜ ፍላጎቷን አሳይታለች። ነገርግን ከታይዋን ጋር ይፋዊ የሆነ ግንኙነት ማድረግ፣ ታይዋንን የራሷ ግዛት አድርጋ ለምትመለከታት ቻይና ቀይ መስመር ነው።
የቀድሞዋ የአሜሪካ አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝነት በሁለቱ ሀገራት ታሪክ ከፍተኛ የሚባል ዲፕሎማሲያ ውጥረት መፍጠሩ ይታወሳል።