የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ራማፎሳ በጎርፍ ለተጎዱ ሰዎች ፀሎት እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ
ፕሬዝዳንቱ “አደጋው በህይወት ዘመኔ ካጋጠሙኝ አሳዛኝ ጊዜያት አንዱ ነው” ብለዋል
በደቡብ አፍሪካ የጎርፍ አደጋ 41 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱ መረጃዎች ይጠቁማሉ
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በሀገሪቱ በጎርፍ ለተጎዱ ሰዎች ጸሎት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
በደቡብ ምስራቅ የባህር ጠረፍ ከተማ በሆነችው ደርባን እና አካባቢው ላይ የደረሰው የጎርፍ አደጋ የበርካቶች ህይወት የቀጠፈ አሳዛኝ ክስተት እንደነበር የሚታወስ ነው።
የሀገሪቱ የነፍስ አድን ሰራተኞች ፍለጋውን በማስፋት ላይ ሲሆን ፤እስካሁን የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 400 ገደማ መድረሱን እና ከዚህም እንደሚችል ሲጂቲኤን ዘግቧል።
በዚህም የጎርፍ አደጋው “በሀገራችን ከዚህ ቀደም አይተነው የማናውቀውና ብዙ ሰዎች የሞቱበት ከፍተኛ መጠን ያለው አደጋ ነው” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ምደቡብ አፍሪካውያን ለተጂዎች እንዲጸልዩ ጥሪ አቅርቧል።
“በኩዋዙሉ-ናታል (አውራጃ) ላሉ ወገኖቻችን አስፈላጊውን ፈውስ እንዲያገኙና ህይወታቸው እንዲቀጥል እንጸልይላቸው” ሲሉም በምስራቅ ኤርሜሎ ከተማ ላሉ የኤል-ሻዳይ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ጠይቋል።
ህጻናትን ጨምሮ 10 አባላትን ያጣ ቤተሰብ መጎብኘታቸውን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ ፤ በተፈጠረው ሁኔታ እጅጉን ማዘናቸውም ገልጿል።
“ በህይወቴ እንዲሁም በፕሬዝዳንትነት ዘመኔ ካጋጠሙኝ አሳዛኝ ጊዜያት አንዱ ነው” ሲሉ ፕሬዝዳንቱ በቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት ባስተላለፉት መልእክት ተደምጠዋል።
የተጎጂዎች ዘመዶች ያጋጠማቸው ስቃይ ለዓመታት የሚቆይ ሊሆን እንደሚችል ያነሱት ፕሬዝዳንቱ፤ ሁሉም ከጎናቸው ሊቆም እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል።
በደቡብ አፍሪካ ያጋጠመው የጎርፍ አደጋ፤ 41 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱ ይታወቃል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች አደጋውን ተከትሎ ሀዘናቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው።