ፕሬዝዳንት ራማፎዛ ባለፈው ዓመት የካቲት ላይ ጆንሰን እና ጆንሰን የተሰኘውን ክትባት ወስደው እንደነበር ተገልጿል
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ከኮሮና ቫይረስ አገግመው ወደ ስራ መመለሳቸውን ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ።
ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ በኬፕታውን የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ደ ክለርክን መታሰቢያ ስነስርዓት ላይ ለመገኘት ከመታሰቢያ አገልግሎት ከወጡ በኋላ ጥሩ ስሜት ሳይሰማቸው ቀርቶ ምርመራ አድርገው ነበር፡፡ በዚህ ምርመራም የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸው ለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩት ፕሬዝዳንቱ አሁን ወደ መደበኛ ስራቸው መመለሳቸውን የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ይፋ አድርጓል፡፡
ፕሬዝዳንት ራማፎዛ ባለፈው ዓመት የካቲት ላይ ጆንሰን እና ጆንሰን የተሰኘውን ክትባት ወስደው እንደነበር ተገልጿል፡፡ ፕሬዝዳንቱ ከኮሮና አገግመው መደበኛ ስራቸው ላይ እንደሆኑ የተገለጸ ሲሆን የአውሮፓውያኑ 2021 የመጨረሻ የካቢኔ ስብሰባም ከነገ በስቲያ እንደሚመሩ ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ ከሰሞኑ ባደረጉት ምርመራም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ ቀለል ያሉ ምልክቶችን ታተውባቸው ህክምና ሲከታተሉ እንደነበር መገለጹ ይታወሳል፡፡
ራማፎዛ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ መንግስታዊ ኃላፊነታቸውን ለአንድ ሳምንት ለምክትላቸው ዴቪድ ማቡዛ በውክልና መስጠታቸው ተገልጾ ነበር።