የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገጻቸው ፕሬዝደንት ኢሳያስ በሩሲያ ፕሬዝደንት ፑቲን ግብዣ ወደ ሩሲያ ማቅናታቸውን ገልጸዋል
የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቻይናን ከጎበኙ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ወደ ሩሲያ አቅንተዋል።
የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስቴር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገጻቸው ፕሬዝደንት ኢሳያስ በሩሲያ ፕሬዝደንት ፑቲን ግብዣ ወደ ሩሲያ ማቅናታቸውን ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ እንደገለጹት ፕሬዝደንት ኢሳያስ ለአራት ቀናት በሩሲያ ይቆያሉ።
ፕሬዝደንቱ ወደ ሩሲያ ሲያቀኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኦስማን ሳልህ እና የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ ዘመዴ ተክል አብረዋቸው እንዳሉ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ፕሬዝደንት ኢሳያሳ ከሁለት ሳምንታት በፊት የሩሲያ አጋር የሆነችውን ቻይናን መጎብኘታቸው ይታወሳል።
ፕሬዝደንት ኢሳያሳ ቻይናን የጎበኙት የቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ዋንግ ዩ ሚያዚያ መጨረሻ በኤርትራ ተገኝተው፣ ቻይናን ኢንዲጎበኙ ጥያቄ ካቀረቡላቸው በኋላ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ፕሬዝደንት ዢ ጅንፒንግ ለፕሬዝደንት ኢሳያሳ ያቀረቡትን የቻይናን ጎብኝ ደብዳቤ ይዘው እንደመጡ ሚኒስትር የማነ በወቅቱ ገልጸው ነበር።
በግብዣው መሰረት ፕሬዝደንት ኢሳያስ ከሁለት ሳምንታት በፊት ቻይና ጎብኝተዋል።
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በቻይና ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ እና ከሀገሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ጋር መምከራቸው ይታወሳል።