የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ፕሬዝዳንት አረፉ
ዩኤኢ የፕሬዝዳንቷን ሞት ተከትሎ ለቀጣዮቹ 40 ቀናት የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ወስናለች
ሼክ ኸሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን ዛሬ አርብ በ73 ዓመታቸው ማረፋቸው ተሰምቷል
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ፕሬዝዳንት አረፉ፡፡
አቡዳቢን ለረጅም ዓመታት በመምራት የሚታወቁት ሼክ ኸሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን በዛሬው ዕለት ማረፋቸውን ጽህፈት ቤታቸው አስታውቋል፡፡
ጽህፈት ቤቱ ባወጣው መግለጫ ሼክ ኸሊፋ በማረፋቸው ማዘኑን በመግለጽ ለተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ ለአረብ እና ለተቀረው ዓለም መጽጽናናትን ተመኝቷል፡፡
በፈረንጆቹ 1948 የተወለዱት ሼክ ኸሊፋ ከ2004 ጀምሮ ሀገራቸውን በፕሬዝዳንትነት በማገልገል ላይ ነበሩ፡፡
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የፕሬዝዳንቱን ሞት ተከትሎ ለቀጣዮቹ 40 ቀናት የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ወስናለች፡፡
በቀጣዮቹ ሶስት ቀናት ስራ ዝግ እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡