ፕሬዘዳንት ትራምፕ እስከ 100ሺ አሜሪካውያን ሊሞቱ ይችላሉ አሉ
የኮሮና ቫይረስ ክትባት በዚህ አመት መጨረሻ ሊገኝ እንደሚችል ፕሬዘዳንት ትራምፕ እምነታቸውን ገልጸዋል
በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ እስከ 100ሺ ሰዎች ሊሞት እንደሚችሉ ፕሬዘዳንት ትራምፕ ገለፁ
በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ እስከ 100ሺ ሰዎች ሊሞት እንደሚችሉ ፕሬዘዳንት ትራምፕ ገለፁ
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንደገለጹት የሟቾቸ ቁጥር ቀድሞ ከገመቱት ከበለጠ በኋላ እስከ 100ሺ የሚደርሱ አሜሪካውያን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሊሞቱ አንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡
ፕሬዘዳንቱ ይሄን ያሉት ፎክስ ኒውስ ላይ ቀርበው በኮሮና ቫይረስ የተጎዳው የአሜሪካ ኢኮኖሚ እንዴት ማገገም እንዳለበት በተነበዩበትና ለወረርሽኙ መስፋፋት ቻይናን በወቀሱበት ጊዜ ነበር፡፡
ነገርግን በዚህ አመት መጨረሻ ክትባት እንደሚገኝ እርግጠኛ አንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ በአሜሪካ እስካሁን 1.1 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁ ሲሆን ከ67ሺ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
“ከ75ሺ እስካ100ሺ ሰዎችን እናጣለን፡፡ ያ በጣም ዘግናኝ ነገር ነው” ያሉት ትራምፕ የሚሞቱት ሰዎች ከዚህ እንደሚያንስ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል፡፡
የኮሮና በሽታ ተጠቂዎች ቁጥር እየቀነሰ በመሄዱና ኢኮኖሚውን በአፍጢሙ በደፋው ኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለችግር የተዳረጉ ሰዎች እርዳት በመፈለጋቸው፣ከግማሽ ባለይ የሚሆኑት የአሜሪካ ግዛቶች የእንቅስቀሴ እግዱን በከፊል እያነሱት ይገኛሉ፡፡
“አንደሀገር ተዘግተን አንቆይም” ብለዋል ዶናልድ ትራምፕ፡፡
የኮሮና ቫይረስ ክትባት በዚህ አመት መጨረሻ ሊገኝ እንደሚችል ፕሬዘዳንት ትራምፕ አምነታቸውን ገልጸዋል፡፡ ወረርሽኑ ሊያገረሽ የሚችልበት እድል ቢኖርም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤትና ኮሌጆች በመህር ወቅት እንዲመለሱ እንደሚፈልጉም ተናግረዋል፡፡