የትራምፕ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ በኮሮና ቫይረስ ተያዙ
የትራምፕ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ በኮሮና ቫይረስ ተያዙ
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ብሄራዊ የደህንነት አማካሪ የሆነው ሮበርት ኦብሪን በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡ ብሉምበርግ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ኦብሪን ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ከቢሮ ውጭ መሆናቸውን አብራርቷል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ ኦብሪን በኮሮና ቫይረስ የተያዘው የቤተሰብ ፕሮግራም ከተካፈሉ በኋላ ሲሆን ብሄራዊ ካውንስሉን ቤታቸው ሆነው በስልክ እየመሩት ይገኛሉ፡፡ ኋይት ሀውስ ይህን በተመለከተ መልስ አለመስጠቱን ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡
ኦብሪን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ የፕሬዘዳንት የቅርብ ሰው መሆኑ ሲታወቅ፣ አሜሪካ አዲስ በቫይረሱ በሚያዙ ሰዎችና በሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየመራች ነው፡፡ኦብሪንና ከፍተኛ ሃላፊዎች በየቀኑ ኮሮና ምርመራ ሲያካሄዱ ነበር፡፡ የኦብሪን ቢሮ ፕሬዘዳንቱ ከሚሰሩበት የኦቫል ቢሮና ምክትል ፕሬዘዳንቱ ማይክ ፔንስ ቢሮ በቅርብ ርቀት ይገኛል፡፡
የጆንሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ እንደሚያሳየው ከሆነ በመላው አለም እስካሁን ከ16 ሚሊዮን ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ፣ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
በአሜሪካ ብቻ 4ነጥብ 2 ሚሊዮን ሰዎቸ በኮሮና ሲያዙከ146ሺ በላይ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን ማጣታቸውን መረጃው ያመለክታል፡፡