አሜሪካ ለዓለም ጤና ድርጅት የምትሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ለምን አቋረጠች?
ፕሬዘዳንት ትራምፕ አሜሪካ ከ400 እስከ 500 ሚሊየን ዶላር በየአመቱ ለድርጅቱ ትረዳለች ብለዋል
አሜሪካ ለዓለም ጤና ድርጅት የምትሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ማቋረጧን ፕሬዘዳንት ትራምፕ አስታወቁ
አሜሪካ ለዓለም ጤና ድርጅት የምትሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ማቋረጧን ፕሬዘዳንት ትራምፕ አስታወቁ
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ለዓለም ጤና ድርጅት የምትሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ማቋረጧን በትናንትናው እለት አስታውቀዋል፡፡
ፕሬዘዳንቱ የአለም ጤና ድርጅት “የኮሮና ቫይረሰ ስርጭትን ሸፋፍኗል፤ በአግባቡም ችግሩን አልመራም” ሲሉ ድርጅቱን መክሰሳቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
ትራምፕ ይህን ያስታወቁት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አለምን እያመሰና ፕሬዘዳንቱም የቫይረሱን ስርጭትን ለመቆጣጠር የሄዱበትን መንገድ በንዴት እየተከላከሉ ባሉበት ወቅት ነው፡፡
ትራምፕ ከራሰቸው አስተዳደር የሚቀርቡ ቅድመ ማስጠንቀቂያዎችን ችላ ብለዋል በሚል የጥያቄ ናደ እየወረደባቸው ሲሆን እሳቸው ግን ለደረሰው ጉዳት ኃላፊነት የሚወስድላቸው የአለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ ሌሎችን እየፈለጉ ነው፡፡
አሜሪካ ከ400 እስከ 500 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በየአመቱ ትረዳለች ያሉት ትራምፕ ቻይና ግን 40 ሚሊዮን ዶላር ነው የምትረዳው ብለዋል፡፡
ድርጅቱ የጤና ባለሙያዎችን ይዞ በቻይና ያለውን ነገር በአግባቡ መመርመር ቢችልና ቻይናም ግልጽ አንድትሆን ጥሪ ቢያቀርብ ኖሮ ቫይረሱን በትንሽ ሞት ከምንጩ ማስቀረት ይቻል ነበር ብለዋል ፕሬዘዳንት ትራምፕ፡፡
ፕሬዘዳንት ትራምፕ አሜሪካ ለተባበሩት መንግስታት የምታደርገውን ድጋፍ ጥያቄ ውስጥ አስገብተዋል፡፡ አሜሪካ ከአለም አቀፉ የአየር ንብረት ስምምነት ራሷን አግልላለች፤ የአለም ንግድ ድርጅት ላይም ጠንካራ ወቀሳ አቅርባለች፡፡