
የላቲን አሜሪካ ሀገራት ስደተኞች በዶናልድ ትራምፕ አስተዳድር ኢላማ ተደርገዋል
ከአሜሪካ ብዙ ስደተኞች የተባረሩባቸው ሀገራት እነማን ናቸው?
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡበት ዕለት ጀምሮ ህጋዊ የመኖሪያ እና ስራ ፈቃድ የሌላቸው ስደተኞችን ኢላማ አድርገዋል።
ይህን ተከትሎ በየዕለቱ የአሜሪካ ጸጥታ ሀይሎች በአማካኝ አንድ ሺህ ስደተኞችን እያሰሩ ሲሆን ስደተኞቹን ወደየመጡባቸው ሀገራት በግድ እየመለሱ ይገኛሉ።
በግድ ወደመጡባቸው ሀገራት ከተመለሱ ዜጎች መካከልም የሞክሲኮ፣ ኮሎምቢያ፣ ጓቲማላ እና ኢኳዶር ደግሞ በአንጻራዊነት ብዙ ዜጎች ተመልሰዋል ሲል ኤንቢሲ ዘግቧል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ስድስት ሺህ ገደማ ስደተኞችን በግድ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል።
የሀገሪቱ መንግሥት ባንዴድ ጊዜ 40 ሺህ ስደተኞችን ማሳደር የሚያስችል አልጋ መገንባቱን እና በቀጣይ ሰፊ ቁጥር ያላቸው ስደተኞችን የማሰር እቅድ እንዳለው በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።