
የሩሲያው ፕሬዝዳት ሃገራቸው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር ማዋሏን አስታወቁ
የሩሲያው ፕሬዝዳት ሃገራቸው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር ማዋሏን አስታወቁ
የቫይረሱን ስርጭት ሙሉ በሙሉ መቆጠጠራቸውን የገለጹት ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሞስኮ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ያደረገችው ጥረት የሚደነቅ መሆኑንም ነው ያስታወቁት፡፡ በሁሉም ደረጃ ያሉ ሰዎች በቁርጠኝት በተቀናጀና ሃላፊነት በተሞላበት መንገድ በመስራታቸው ኮሮና ቫይረስን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ገልጸዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡
ቭላድሚር ፑቲን የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት ለኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ሩሲያውያን ባስተላለፉት መልዕክት ሃገራቸው ችግሮችን ለመቋቋምና ክብሯን ለመጠበቅ ዝግጁ ናት ብለዋል፡፡
ሩሲያ የሌሎች ሃገራትን ልምድ በመቅሰም ወረርሽኙን ለመከላከል ከፍተኛ ትግል አድርጋለች ብለዋል፡፡ ከውጭ ሃገራት ወዳጆቻችን ጋር በመሆን አሁን ላይ ምን መደረግ እንዳለበት እየተነጋገርን ነው ያሉት ፕሬዝዳቱ ጉዳቶችን ለመቀነስና ቫይረሱ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ እየሰራን ነው ብለወላ፡፡
ሲጂቲኤን የክሬምሊን ዌብሳይትን በመጥቀስ፣ ፕሬዝዳንቱ ሀገራቸው ቫይረሱን ተቆጣጥራለች ማለታቸውን ከመዘገቡ ዉጭ ለመቆጣጠራቸው ማሳያው ምን እንደሆነ ግን ያለው ነገር የለም፡፡
በሩሲያ እስካሁን ከ42 ሺ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን 361 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡ በመላው ዓለም ደግሞ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ2.3 ሚሊዮን በላይ ደርሷል፡፡