ቻይና “የኢትዮ-ቻይና ግንኙነት ጠንካራና የማይሰበር ነው” ማለቷን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ
ም/ጠሚና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመከቀ ከቻይና አቻቸው ጋር ተወያይተዋል
ኢትዮጵያ፣ቻይና የኢትዮጵያ ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት እንዲጠበቅ ለምታሳየው ቁርጠኝነት አድናቆት እንዳላት መግለጫው ጠቅሷል
የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤የኢትዮጵያና የቻይና ግንኙነት “ጠንካራና የማይሰበር ነው" ማለቷን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ ለስራ ጉብኝት በትናንትናው እለት አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን በዛሬው እለት ከኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
ሚኒስትር ዋንግ ይ በአዲስ አበባ ጉብኝት ማድረጋቸው፣ ቻይና በኢትዮጵያ ላይ ያላትም እምነትና ለኢትዮጵያ መንግስት ያላትን ድጋፍ ለመግለጽ ነው ማለታቸውን መግለጫው ጠቅሷል፡፡
መግለጫው እንዳለው በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚደረግ ማንኛውንም አይነት ጣልቃ ገብነት ቻይና እንደምትቃወም ተገልጿል፡፡
ከኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ ቻይና ከኢትዮጵያ የምታደርገውን መርህን መሰረት ያደረገ ግንኙት አድንቀዋል፡፡
ሚኒስትሩ ቻይና ለኢትዮጵያና የግዛት አንድነት እንዲጠበቅ ለምታሳየው ቁርጠኝነት እንደሚያደንቁ መግለጫው ጠቅሷል፡፡
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወደ ኢትዮጵያ የመጡት፤ የኢትዮጵያ መንግስት አሜሪካና አንዳንድ የምእራብ ሀገራት በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት በተመለከተ አላስፈላጊ ጫና አሳድረውብናል እያላ ባለበት ወቅት ነው፡፡
በአሜሪና በሌሎች ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውን፣ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጣልቃገብነት የሚቃወም ሰልፍ በቅርቡ ማካሄዳቸው ይታወሳል፡፡
በፌደራል መንግስትና በህወሃት ሃይሎች መካከል ያለው አለመግባባት ወደ ወታደራዊ ግጭት ከገባ ከ8 ወራት በኋላ ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም አውጆ፤ጦሩን ከትግራይ ክልል ማስወጣቱ ይታወሳል፡፡
ነገርግን በኢትዮጵያ መንግስት በሽብር የተፈረጀው ህወሃት በአማራና አፋር ክልሎች ጥቃት መክፈቱንና ይህንም ለመቀልበስ እንደሚንቀሳቀስ መንግስት መግለጹ ይታወሳል፡፡
በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል ውስጥ በመንግስት እና በህወሓት ኃይሎች መካከል ጦርነት እየተካሄ የሚገኝ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ጦር ግንባር ዘምተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ከግንባር ሆነው ባስተላለፉት መልእክት፤ ጦርነቱን መንግስት ማሸነፉ የማይቀር ስለሆነ የህወሓት ታጣቂዎች እጃቸውን ለጸጥታ አካላት እንዲሰጡ ጥሩ በትናንትናው እለት ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡