የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ የ“ሩሲያ ወረራ” እስካሁን 400 ገደማ ሆስፒታሎችን አውድሟል አሉ
መጋቢት 9 ቀን፤ በተከበበቸው የማሪፖል ከተማ የወደመው የእናቶች ሆስፒታል ጦርነቱ በጣም ከተወገዘባቸው ድርጊቶች አንዱ ነው
የክሬምሊን ሰዎች ግን “በዚህ ጦርነት ዒላማ የምናደርጋቸው የተመረጡ ወታደራዊ ስፍራዎችን ነው ብለዋል
የሩሲያ ወረራ 400 ገደማ የዩክሬን የጤና ተቋማት ማውደሙና የህክምና ባለሙያዎች ህክምና ለመስጠት የሚያስችላቸው የህክምና ቁሳቁስ ማጣታቸው፤ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮልድሚር ዘለንስኪ ገለጹ፡፡
ዘለንስኪ በምስራቅ እና ደቡባዊ ዩክሬን ዋና ዋና የጦር ሜዳዎች ውስጥ የሚገኙ የጤና ተቋማት፤ ሌላው ቢቀር መሰረታዊ አንቲባዮቲኮች እንኳን የላቸውም ብለዋል፡፡
ሩሲያ በአንድ ሌሊት 389 የዩክሬን ወታራዊ ኢላማዎችን መምታቷን ገለጸች
ን"የሩሲያ ወታደሮች የህክምና መሰረተ ልማቶችን ብቻ ከግምት ውስጥ በማስገባት ፤ ወደ 400 የሚጠጉ ሆስፒታሎች በማውደም ላይ ናቸው" ሲሉም ነው ዘለንስኪ በትናንትናው እለት ከህክምና በጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር በበይነ መረብ በነበራቸው ቆይታ የተናገሩት ።
በተለይም በሩሲያ ወታደሮች በተያዙ አካባቢዎች ያለው ሁኔታ እጅግ የሚያስጨንቅ ነውም ብሏል ፕሬዝዳንቱ፡፡
"የካንሰር በሽተኞች መድሃኒት ሊያገኙ አልቻሉም፤ በሌላ አገላለጽ ለስኳር በሽተኞችም ከባድ የኢንሱሊን እጥረት አለ ማለት ነው፤ ቀዶ ጥገና ለማድረግም እንዲሁ የማይቻል ነው ሲሉም ያለውን ችግር ገልጸውታል ዘለንስኪ፡፡
እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ፤ መጋቢት 9 ቀን፤ በተከበበቸው የማሪፖል ከተማ የወደመው የእናቶች ሆስፒታል ጦርነቱ በጣም ከተወገዘባቸው ድርጊቶች አንዱ ነው፡፡
ሩሲያ ግን ጥቃቱን የሚያሳይ ፎቶ የተቀነባበረ ነው ስትል ክሱን ውድቅ አድርገዋለች፡፡
የክሬምሊን ሰዎች፤ እኛ በዚህ ጦርነት ዒላማ የምናደርጋቸው የተመረጡ ወታደራዊ ስፍራዎችን እንጂ ሲቪልያን አይደለም ሲሉም ተደምጧል፡፡
ዩክሬን በየቀኑ ከሩሲያ ጦር መሳሪያዎች የተጎዱትን ሲቪሎች ሪፓርት ስታቀርብ እንዲሁም ሩሲያ ውንጀላዎችን ውድቅ ስታደርግ መስማት በዚህ ጦርነት የተለመደ ሆኖ ቀጥሏል፡፡
የዶኔትስክ አስተዳዳሪ ፓብሎ ኪሪሬንኮ ፤ በባቡር ጣቢያ በተወረወረ ቦምብ ከ50 በላይ ሰዎች መሞታቸው 25 ሰዎች መቁሰላቸው እንዲሁም 32 ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱ ባለፈው ወር መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡
ሩሲያ 'ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ' ብላ የምትጠራው ነገር ግን በምዕራቡ ዓለም ወደ “ጦርነት” ደረጃ ከፍ ያለ እንደሆነ የሚነገርለት ፤ የዬክሬን ጦርነት በሚልዮኖች የሚቀጠሩ ሲቪሎችን ለእንግልት መዳረጉ እንደቀጠለ ነው፡፡