ሩሲያ በአንድ ሌሊት 389 የዩክሬን ወታራዊ ኢላማዎችን መምታቷን ገለጸች
ሩሲያም ምእራባውያን ሀገራት ከሩሲያ ለሚገዙት ጋዝ በሩብል እዲከፍሉ መወሰኗ አበሳጭቷቸዋል
አሜሪካን ጨምሮ ምእራባውያን ሀገራት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ድጋፍ በማድረግ ላይ ናቸው
ሩሲያ በዛሬው እለት 389 የሚሆኑ የዩክሬን ወታደራዊ ኢላማዎችን በአንድ ሌሊት መምታቷን አስታውቃለች፡፡
የሩሲያ ጦር የከባድ መሳሪያ ቡድን 35 የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎችን፣ 15 የከባድ ጦር መሳሪያ እና ተተኳሽ፤ የዩክሬን ወታደሮችና መሳሪያዎች የተከማቹባቸውን ጨምሮ 389 ወታደራዊ ኢላማዎችን መምታቷን ገልጻለች፡፡
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር የሩሲያ ጦር አራት የጦር መሳሪያ ዲፕት እና የነዳጅ ማከማቻን አወደመች ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ነገርግን ሮይተረስ ሩሲያ 389 ወታደራዊ ኢላማዎች መምታቷን ማረጋገጥ አይቻልም ብሏል፡፡
ሩሲያ ጎረቤቷ ዩክሬን ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከፈረንጆች የካቲት 24፤ 2022 ጀምሮ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄድ መጀመሯ ይታወቃል።
በየሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት ከ5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ሀገራቸውን ለቀው ወደ ጎረቤት ሀገራት ተሰደዋል፡፡ ሩሲያ በዩክሬን ላይ እየወሰደች ያለውን ወታደራዊ እርምጃ ከጀምሩም ቢሆን የተቃወሙት ምዕራባውያን፤ ሩሲያን ያዳክማሉ ያሉዋቸው ማዕቀቦች ሲጥሉ እየተስተዋሉ ነው።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ ባደረገው ስብሰባ ሩሲያ ዩክሬንን መዉረሯን የሚያወግዘዉን የዉሳኔ ሀሳብ በአብላጫ ድምጽ ማጸደቁም እንዲሁ የሚታወስ ነው።
የተመድ ጠቅላላ ጉባኤም ሩሲያ ተመድ የሰብአዊ መብት ምክርቤት በአብላጫ ድምጽ እንድትታገድ ያደረገ ሲሆን ሩሲያም ይህን ተከትሎ ከም/ቤቱ አባልነት መውጣቷን ማስታወቋ ይታወሳል፡፡
ሩሲያ ከም/ቤቱ የታገደችው ሩሲያ ጦር በዩክሬን ባካሄደው ጦርነት፣በሰብአዊነት ላይ ወንጅል ፈጽሟል በሚል ነበር፡፡
ፑቱን በዩክሬን “ወታደራዊ ዘመቻ” ለማድረግ የተገደዱት፤ አሜሪካ ዩክሬንን እና ኔቶን በመጠቀም ለማስፈራራት ስለሞከረች እና ይህንም መከላከል ሲለሚገባ ነው ብለዋል፡፡
ፕሬዝደንት ፑቲን ሩሲያ በዩክሬን ሁሉንም የምትፈልገውን አላማ ታሳካለች ብለዋል፡፡
በቅርቡ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ባካሄደው ስብሰባ ሩሲያን ከተመድ የሰብአዊ መብቶች ም/ቤት ማስወጣቱ ይታወሳል፡፡ ጉባኤው በአብላጫ ድምጽ ሩሲያ ያገደው የሩሲያ ወታደሮች በዩክሬን በሰብአዊ መብት ላይ ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ነበር፡፡
ይህን ውሳኔ ተከትሎ ሩሲያ ከተመድ የሰብአዊ መብቶች ም/ቤት አባልነት ወጥታለች፤ሩሲያ የአምነስቲ እንተርናሽናል እና የሂውማን ራይትስ ዎች ቢሮዎችንም ዘግታለች፡፡ አሜሪካን ጨምሮ ምእራባውያን ሀገራት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ድጋፍ በማድረግ ላይ ናቸው፤ ሩሲያም ምእራባውያን ሀገራት ከሩሲያ ለሚገዙት ጋዝ በሩብል እዲከፍሉ ማድረጓ አበሳጭታቸዋል፡፡