የሶማሊላንድ የምርጫ ኮሚሽን ምርጫው የሚካሄድበትን ጊዜ በዘጠኝ ወራት አራዝሟል
በተገንጣይ ሶማሊላንድ ሊካሄድ የነበረው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ “በቴክኒካል እና በፋይናንሺያል ምክንያቶች” መራዘሙን ምርጫ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
ሙሴ ቢሂ አብዲ በፈረንጆቹ 2017 በአፍሪካ ቀንድ ራሱን እንደሀገር የሚቆይረው ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡ ሲሆን ምርጫው የስልጣን ዘመናቸው ከማለቁ ከአንድ ወር በፊት ህዳር 13 ቀን እንዲደረግ ታቅዶ ነበር።
የምርጫ ኮሚሽኑ ኃላፊ ሙሴ ዩሱፍ ግን ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ጉዳዮች ምርጫው ሊካሄድ አልቻለም ብለዋል።
ዩሱፍ በዋና ከተማው ሃርጌሳ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት የምርጫ ዝርዝሮች ገና መዘጋጀታቸውን እና "በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ምርጫውን ማደራጀት አይቻልም" ብለዋል፡፡
ኮሚሽኑ ምርጫው ለካሄድ የሚችልበትን ቀን ባይቆርጡም “ከፈረንጆቹ ጥቅምት 1፣ 2022 ጀምሮ ለዘጠኝ ወራት መዘግየት” ብቻ ይኖራል ብሏል።
የተቃዋሚ ፓርቲ እጩ ፋይሰል አሊ ወራቤ የምርጫ ኮሚሽኑን ውሳኔ ደግፈዋል።
የፕሬዚዳንቱን የስልጣን ማራዘሚያ ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆናቸውን በትዊተር ገፃቸው የገለጹት ፋይሰል አሊ ወራቤ ኮሚሽኑ ምርጫውን ለዘጠኝ ወር ማራዘሙን ደፍገዋል፡፡
የፖለቲካ ተንታኝ ባርካድ እስማኤል ግን የሕግ አውጭ አካላት “ምናልባት በሚቀጥሉት ሳምንታት የፕሬዚዳንቱን የስልጣን ጊዜ ሊያራዝሙ ነው” ብለዋል።
ባለፈው ወር መጀመሪያ ላይ ፖሊስ መንግስትን የሚቃወሙ ተቃዋሚዎችን በጥይት በመተኮሱ የበርካታ ሰዎች መግደሉን እና በደርዘን የሚቆጠሩ መቁሰላቸውን የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት እና እማኞች ተናግረዋል፡፡
ተቃዋሚዎች የሶማሊላንድ መንግስት ምርጫውን ለማራዘም አቅዷል የሚል ክስ ማቅረባቸውን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለተቃውሞ አደባባይ መውጣታቸው ይታወሳል፡፡