የወታደሮቹን ግድያ ተከትሎ ባይደን ኢራንን በቀጥታ እንዲደበድቡ ጫና እየተደረገባቸው ነው
የአሜሪካ ወታሮች መገደል ፕሬዝዳንት ባይደን በቀጥታ ኢራንን ኢንዲያጠቁ የሚደረጉ ጫናዎች እንዲጨምሩ አድርጓቸዋል ተብሏል
ፕሬዝደንቱ ግን የጦርነቱ አድማስ ይሰፋል በሚል ስጋት በቀጥታ በኢራን ላይ ጥቃት ለመክፈት ፍላጎት እንደሌላቸው ተገልጿል
የአሜሪካ ወታደሮች መገደላቸውን ተከትሎ ባይደን ኢራንን በቀጥታ እንዲደበድቡ ጫና እየተደረገባቸው ነው ተብሏል።
በዮርዳኖስ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 3 የአሜሪካ ወታደሮች መገደላቸውን እና ሌሎች 34 ወታደሮች ደግሞ መቁሳለቸውን ፕሬዝደንት ባይደን አስታውቀዋል።
ፕሬዝደንቱ እንዳሉት ጥቃቱ የተፈጸመው በኢራን በሚታገዙ ታጣቂ ኃይሎች ነው።
የአሜሪካ ወታደሮች መገደል ፕሬዝዳንት ባይደን በቀጥታ ኢራንን ኢንዲያጠቁ የሚደረጉ ጫናዎች እንዲጨምሩ ማድረጋቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ፕሬዝደንቱ ግን የጦርነቱ አድማስ ይሰፋል በሚል ስጋት በቀጥታ በኢራን ላይ ጥቃት ለመክፈት ፍላጎት እንደሌላቸው ተገልጿል።
ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ አሜሪካ የአጸፋ ምላሿን ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ በታጣቂዎቹ ላይ ብቻ ልታደርግ ትችላለች።
የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ከተጀመረበት ከባለፈው የፈረንጆቹ አመት ጥቅምት 2023 ወዲህ የአሜሪካ ኃይሎች በኢራን በሚደገፉ ኃይሎች በኢራቅ፣በሶሪያ፣በጆርጃን እና በየመን የባህር ጠረፍ 150 ጊዜ ጥቃት ደርሶባቸዋል።
ነገርግን በትናንትናው እለት ጆርዳን ከሶሪያ በምትዋሰንበት ሰሜንምስራቅ ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው 'ታወር 22' ከደረሰው ጥቃት በፊት የአሜሪካ ወታደር ቆስሎም ሆነ ተገድሎ አያውቅም ነበር።
ፕሬዝደንት ባይደን ከኢራን ጋር ቀጥተኛ የሆነ ግጭት ውስጥ ሳይገቡ በኢራን የሚደገፉ ኃይሎችን መበቀል ይፈልጋሉ።
ባይደን ዝርዝር ባይሰጡም፣ አሜሪካ ምላሽ ትሰጣለች ብለዋል።
ሪፐብሊካኖች ፕሬዝደንት ባይደን የአሜሪካ ወታሮች ያለተከላካይ እንዲቀሩ እያደረጓቸው ነው የሚል ትችል እያቀረቡ ናቸው።
በምላሹ ባይደን ኢራንን መደብደብ አለባት ሲሉ ሪፐብሊካኖች ተናግረዋል።
በአሜሪካ የወካዮች ምክርቤት ወይም ኮንግረስ የአሜሪካ ጦር ተቆጣጣሪ ኮሚቴን የሚመሩት የሪፐብሊካን ተወካይ ማይክ ሮገርስ በኢራን ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርበዋል።
"ፕሬዝደንት ባይደን አሸባሪውን የኢራን መንግስት እና አክራሪ የሆኑ አጋሮቹን ተጠያቂ የሚያደርግበት ጊዜው አልፏሌ" ብለዋል ሮገርስ።
ኢራን በበኩሏ በአሜሪካ ወታደሮች ግድያ እጇ እንደሌለበት ገልጻለች።