ትውልደ አሜሪካዊቷ ልዕልት ሉዶቪሲ በጣሊያን ከሚኖሩበት ቪላ ለቀው እንዲወጡ ታዘዙ
ቪላው የጣሊያናዊው እውቅ ሰአሊ ካርቫጂዮ የግድግዳ ስእል የሚገኝበት ሲሆን፥ እስከ 380 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ ነው
ልዕልቷ ከመኖሪያቸው እንዲወጡ የተነገራቸው የቪላው ውጫዊ ግድግዳ በከፊል ፈራርሶ መንገድ በመዝጋቱ ነው ተብሏል
በዓለም ላይ የሚታወቀውን ብቸኛ የግድግዳ ስዕል የሚያሳይ የሮማውያን ቪላ ውስጥ የሚኖሩት ትውልደ አሜሪካዊቷ ልዕልት ቦንኮምፓኒ ሉዶቪሲ ከሚኖሩበት ቤት ለቀው እንዲወጡ የሚያስገድድ ሁኔታ ገጥሟቸዋል፡፡
ልዕልቷ የሚኖሩበት ቪላ "ካሲኖ ዴል አውሮራ" ታዋቂው ጣሊያናዊው ብቸኛ የግድግዳ ስእል የሚገኝበት ነው።
ይህ ቪላ ውጫዊ ግድግዳው በከፊል ፈራርሶ በአቅራቢያው ያለ መንገድ እንዲዘጋ ማድረጉ ተከተሎ ነው ልዕልቷ ለቀው እንዲወጡ የሮም ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሰጣቸው፡፡
በዚህም ልዕልቷ በሁለት ወራት ውስጥ ንብረታቸው እንዲያስወጡ መታዘዛቸውን ፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡
ቦንኮምፓግኒ ሉዶቪሲ በበኩላቸው ቤቱን ለመልቀቅ የተሰጠኝ የ60 ቀናት ገደብ “አስደንግጦኛል” እናም ይግባኝ መጠየቄ አይቀርም ሲሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡
ልዕልቷ ቤቱን በጨረታ ለመሸጥ በሚል ያለፍቃድ ለጉብኝት ክፍት ማድረጋቸውና ከእንጀራ ልጆቻቸው ጋር ያለው የውርስ ጠብ ጉዳይ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ ላይ ተጽእኖ ፈጥብኛል የሚል እምነት አላቸው፡
ቤቱን ለጎብኚዎች ክፍት ያደረጉት ለቤቱ ጥገና የሚሆን ገንዘብ ለማሰባሰብ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
ካሲኖ ዴል አውሮራ በመባል የሚታወቀው የልዕልቷ መኖሪያ በትንሹ 350 ሚሊዮን ዩሮ (380 ሚሊዮን ዶላር) የመጫረቻ ዋጋ ያለው ሲሆን ይህም በዓለም ላይ ካሉ በጣም ውድ ቤቶች ውስጥ አንዱ ሊሆን እንደሚችል ይታመናል፡፡
የቀድሞ ተዋናይቷና ሞዴል ልዕልት ቦንኮምፓኒ ሉዶቪሲ የቀድሞ የአሜሪካ ኮንግረስ ባለቤት፣ የኒውዮርክ የሪል እስቴት ደላላና በ2009 ከአውሮፓ የከበሩ ቤተሰቦች አንዱ የሆኑት ልዑል ኒኮሎ ቦንኮምፓኒ ሉዶቪሲ ሚስት እንደነበሩ አይዘነጋም።
ይሁን እንጅ ልዑሉ እንደፈረንጆቹ በ 2018 መሞታቸውን ተከተሎ መኖሪያቸው የነበረውን 2ሺህ 800 ካሬ ሜትር ቪላ ሽያጭ ጋር በተያያዘ ከሶስት የእንጀራ ልጆቻቸው ጋር በውርስ ጠብ ውስጥ ገብተው መቆየታቸው ይታወቃል።