ኢትዮጵያ ያላት ግዙፉ C-130 ሄርኩለስ ወታደራዊ አውሮፕላን እውነታቸዎች
ባለ አራት ሞተሩ C-130 ሄርኩለስ ግዙፍ ወታደራዊ አውሮፕላን በሰዓት ከ550 ኪሎ ሜትር በላይ ይከንፋል
ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ30 በላይ ሀገራት ይህንን አውሮፕላን ይጠቀሙበታል
ስለ ግዙፍ ወታደራዊ አውሮፕላን ሲነሳ ግዙፉ C-130 ሄርኩለስ ወታደራዊ አውሮፕላን ቀዳሚው ነው።
ሄርኩለስ ወታደራዊ አውሮፕላን በፈረንጆቹ ከ1956 ጀምሮ በአሜሪካኑ ሎክሂድ ማርቲን ኩባንያ መመረት መጀመሩን መረጃዎች ያመላክታሉ።
ባለ አራት ሞተሩ C-130 ሄርኩለስ የተሰኘው ግዙፍ ወታደራዊ አውሮፕላን ለማረፍም ሆነ ለመነሳት በወጉ የተሰናዳ የመንደርደሪያ ቦታ አይፈልግም።
ሲፈበረክ አላማው የነበረው ወታደሮች፥ ቁስለኞች፥ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ለማመላለስ ቢሆንም በጊዜ ብዛት ግን ለሌሎች አላማዎችም መዋል ችሏል።
ለምሳሌ ለአየር ላይ ወታደራዊ ጥቃት፥ ለህይወት አድን ዘመቻዎች፥ ለሳይንሳዊ ምርምሮች፥ ለአየር ፀባይ ቅኝት፥ ከአውሮፕላን ወደ ሌላ አውሮፕላን አየር ላይ ነዳጅ ለማስተላለፍ፥ ለእሳት አደጋ ማጥፊያ እና ሌሎችም።
አሁንም ድረስ ግን ከሁሉም ተግባራቶቹ በላይ ወታደራዊ ቁሶችን ከቦታ ቦታ በብዛት ለማዘዋወር አገልግሎት ላይ ይውላል።
ግዙፉ C-130 ሄርኩለስ ወታደራዊ አውሮፕላን የተለያዩ አይነት ስሪቶች ያት ሲሆን፤ በአየር ላይ እቃ ለማጓጓዝ እንዲሁም ለኤሌክትሮኖክስ ወይም የአየር መጎድ ስለላ የሚውሉ ናቸው።
ሄርኩለስ AC-130A/E/H/J/U/W የተባው ስሪት የጦር መሳሪያዎች በላዩ ላይ የተገጠመለት እና ለረጅም ጊዜ በአየር ላይ በመቆየት ጥቃት መሰንዘር የሚችል ነው።
ግዙፉ C-130 ሄርኩለስ አምስት የበረራ አባላት ይዞ የሚንቀሳቀስ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 2 አብራሪዎች፣ አንድ ናቪጌተር፣ አንድ የበረራ ኢንጂነር እና አንድ የችነት አስተባባሪ ነው።
19 ሺህ ኪሎ ግራም ጭነት የመሸከም አቅም ያለው ሲሆን፤ ከመሬት በ6 ሺህ 100 ሜትር ከፍታ ላይ የመብረር አቅም እንዳለውም ይነገራል።
በሰዓት ከ550 ኪሎ ሜትር በላይ መብረር የሚችለው አውሮፕላኑ፤ ያለማቋረጥ 3 ሺህ 800 ኪሎ ሜትር ርቀት የመብረር አቅም ያለው መሆኑም ተመላክቷል
ከ30 በላይ ሀገራት ይህንን አውሮፕላን ለወታደራዊ አግግሎት የሚጠቀሙበት ሲሆን፤ አውሮፕላኑን ከታጠቁት ውስጥ የኢትዮጵያ አየር ኃይል አንዱ ነው።