ሴት ጀርባ አካኪዎችን የያዘው የዓለም የመጀሪያው የጀርባ ማከክ ቴራፒ ስቱዲዮም አገልግሎእ እየሰጠ ነው
በሰዓት 130 የአሜሪካ ዶላር ወይም 16 ሺህ ብር በመክፈል ጀርባ ማሳከክ ይቻላል ይላል ከሰሞኑ ከወደ አሜሪካ የተሰማ ዜና።
በሰዎች ዘንድ ስራ ይሆናል ተብለው የማይታሰቡ ተግራት በተለያዩ ጊዜያት ወደ ስራ ተቀይረው ለሰዎች መተዳደሪያ ገቢ ሲያስገኙ ይሰማል።
ከእነዚህም ውስጥ ለመታቀፍ ወፍራም ሰዎችን በሰዓት ከመከራየት ጀምሮ ተከፍሏቸው አልጋ እስከሚያሞቁ ሰዎች ድረስ ገቢ የሚያስገኙ ያተለመዱ ስራዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
ከሰሞኑ ከወደ አሜሪካ የተሰማው ወሬ ደግሞ ባለሙያ ሴቶች የሰዎች ጀርባ በማከክ በሰዓት 130 ዶላር ወይም 16 ሺህ ብር እያገኙ ነው ይለናል።
በዓለማችን የመጀመሪያው ፕሮፌሽናል ጀርባ የማከክ አገልግሎት በ55 ዓመቷ ቶኒ ጆርጅ የተመሰረተ ሲሆን፤ ሙሉ በሙሉ ሴት አካኪዎችን የያዘው የዓለም የመጀሪያው የጀርባ ማከክ ቴራፒ ስቱዲዮም አገልግሎእ እየሰጠ ነው ተብሏል።
ቶኒ ጆርጅ ስራውን እንዴት እንደጀመረች ስትናገርም “ጀርዬን ሲታከክልኝ በጣም ነው የሚያሰደስተኝ፤ ይህ ነገር ሌሎች ሰዎች እንደሚያሰደስት በመረዳት ወደ ስራ ለመቀየር ወሰንኩ” ትላለች።
የሰዎችን ጀርባ ለማከክ እስከ 3 ኢንች የሚረዝም አርቴፊሻል ጥፈር እንደምትጠቀም የተናገረቸው ጆርጅ፤ የሰዎችን ጀርባ ስታክ በሰዓት እስከ 130 ዶላር እንደምታስከፍል ተናግራለች።
ፕሮፌሽናል ጀርባ አካኪ ሴቶች፤ የደንኛቸውን ጀርባ በጥፍራቸው ጫፍ በቀስታ ከላይ እከ ታች የሚያኩ ሲሆን፤ ይህም ደንበኞቻቸው የጭንቀት ስሜት እንዲለቃቸው በማድረግ ዘና እንዲሉ ይረዳቸዋል ተብሏል።
ቶኒ ጆርጅ ስለ አዲሱ ስራዋ ስትናገርም “በሰዎች ዘንድ ያለው ተቀባይነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል” ብላለች።
ቶኒ ከጀርባ አከካ ባለሙያዎቿ ጋር በመሆን ከደንበኞች በሚቀርብላት ጥሪ መሰረት አገልግሎት ለመስጠት እንደ ኒው ዮርክ፣ ሎስ አንጀለስ እና ፊላዴልፊያ ያሉ ትላልቅ የአሜሪካ ከተሞች እንደመትሄድም ተናግራለች።