አቃቤ ህግ ጥፋተኛ የተባሉት “የሆቴል ሩዋንዳ” ጀግና የእድሜ ልክ እስራት እንዲፈረድባቸው ጠየቀ
ሩዘሳባግና ከሁለት አመታት በፊት ነበር በሸብርተኝነት የተከሰሱት
የሩዋንዳ መንግስት አቃቤ ህግ ቀደም ሲል በሩዘሳባግ የተላለፈው የ25 አመት እስራት በቂ አይደለም ብሏል
“ሆቴል ሩዋንዳ” በተባለው ፊልም ላይ በፈረንጆቹ 1994 በተካሄደው የሩዋንዳ የዘርማጥፋት ወቅት በ100 የሚቆጠሩ ሰዎች ያስጠጋው ፓል ሩዘሳባግና የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲፈረድባቸው የሩዋንዳ አቃቤ ህግ ጠይቋል፡፡
ፓል ሩዘሳባግና አሁን ላይ የ25 አመት እስራት ተፈዶሮባቸዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የ67 አመቱ ሩዘሳባግና የፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜን መንግስት የሚቃወም ቡድነን ከማደረጀት ጋር በተያያዘ ባለፈው በፈረንጆቹ መስከረም ስምንት የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ነበር፡፡
የቀረቡባቸውን ሁሉንም ክሶች መነሻቸው ፖለቲካዊ ነው በማለት ያጣጣሉት ሩዘሳባግና በፍርድ ሂደቱ ላይ ለመገኘት ፍቃደኛ አልሆኑም፡፡ ሩዘዛባግና አቃቤ ህግ የእስር ጊዜው እንዲራዘም በሚጠይቅበት በትናንትናው አለት በነበረው የፍ/በት ውሎ አልተገኙም፤ እስርቤት መሆንን መርጠዋል፡፡
የሩዋንዳ መንግስት አቃቤ ህግ ቀደም ሲል በተላለፈው የ25 አመት እስራት ፍርድ እንደማይስማማ አቤቱታውን አሰምቷል፡፡
የሩዘሳባግናን ክስ አስፈላጊነት እና የእነዚህን አይነት ወንጆች በህዝብ ላይ የሚያሳድረውን ጉዳት ያነሳው አቃቤ ህግ፤ እንዲህ አይነት ቀላል ቅጣት ሊጣልበት አይገባም ብሏል፡፡
በሩዋንዳ በፈረንጆቹ 1994 የተካሄደውን ዘርማጥፋት አስመልክቶ በተሰራው “ሆቴል ሩዋንዳ” ፊልም ላይ እንደ ጀግና የተወደሱት ፓል ሩዘሳባጊናን በሽብር ክስ መያዟን አስታውቋለች፤ በካቴና በማሰር በሚዲያ ፊትም ማቅረቧ ይታወሳል፡፡
ለአመታት ሲፈለፍ የነበረው ፓል ሩዘሳባጊና ከ2 አመታት በፊት በፈረንሳይ ተይዘው፤ ፈረንሳይም ለሩዋንዳ አሳልፋ ሰጥታለች፡፡