የብልጽግና ፓርቲ የዕውቅና ምስክር ወረቀት እንዲሰጠው ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቀረበ
በቅርቡ ውህደት የፈጸሙት የኢህአዴግ እህትና አጋር ፓርቲዎች በኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የውህደቱ አካል ለሆኑት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ በፊት ተሰጥቶ የነበረውን የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሰርዝ ጥያቄ አቅርቧል፡፡
በምትኩም ቦርዱ በአዋጅ ቁጥር አንቀጽ 91(4) ሀ መሰረት በውህደት የተመሰረተውን የብልጽግና ፓርቲን እንዲመዘገብና ዕውቅና እንዲሰጠው በመጠየቅ፣ ለዚህ የሚያስፈልጉ ሰነዶችን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቅረቡን ኢህአዴግን በምንጭነት ዋቢ አድርጎ ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ከኢህአዴግ አራት እህት ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በአዲሱ ውህድ ፓርቲ እስካሁን ራሱን አላካተተም፡፡
ምንጭ፡- ኢቢሲ