የቻይና ዜሮ-ኮቪድ ፖሊሲ ሀገሪቱ ከዓለም የተገለለች እንዳያደርጋት ተሰግቷል
የቻይና መሪዎችን ያስደነገጠው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው
ቻይና በሰዎች ህይወት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ማንኛውንም ወረርሽኝ በፍጥነት ለማስወገድ በሚል የ“ዜሮ-ኮቪድ ፖሊሲ”ን ተግባራዊ ስታደረግ መቆየቷ ሚታወቅ ነው፡
ይሁን እንጅ የቻይና መንግስት ኮቪድን ለመቆጠጣር የተከተለው “የዜሮ-ኮቪድ ፖሊሲ”ን ተከትሎ በሀገሪቱ ዜጎች ላይ የተጣለው እገዳ በርካታ የሀገሬው ሰዎች እንዳስቆጣ እንየተነገረ ነው፡፡
ቁጣው በተለይም አሁን ወደ ተቃውሞ ተሸጋግሮ የቻይና መሪዎች ሳያስደነግጥ አልቀረም ይላል የኤኤፍፒ ዘገባ፡፡
ሰልፈኞቹ የተጣለውን እገዳ በሚጥስ መልኩ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ጎዳናዎችና ዩኒቨርስቲዎች ላይ የተቃውሞ ድምጾች ሲያሰሙም ተሰምተዋል፡፡
በተለይም በሻንጋይ ከተማ በነበረው የተቃውሞ ሰልፍ የቻይና መሪ ዢ ጂንፒንግ ከስልጣን እንዲወርዱ ጭምር የተጠየቀበት ነው ተብሏል፡፡
አንድ ሰልፈኛ በተደጋጋሚ "ዢ ጂንፒንግ!" ሲል፤ ሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ "ከስልጣን ውረድ !" ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
በቻይና ህግ የሀገሪቱን መሪ ማውገዝና መሳደብ ወህኒ ቤት ጭምር ሊያስገባ የሚችል አደገኛ ነገር መሆኑ ይታወቃል፡፡
ቻይናውያን “የዜሮ-ኮቪድ ፖሊሲ”ን ቢቃወሙም፤ የሀገሪቱ መንግስት የተከተለው ፖሊሲ ውጤታማ እንደሆነ በቅርቡ መግለጹ ይታወሳል፡፡
የቻይና ገዢ ፓርቲ የሆነው ኮሚኒስት ፓርቲ ቃል አቀባይ ሱን ዬሊ በቅረቡ በቤጂንግ በተካሄደው የፓርቲውን 20ኛ ጉባኤ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፤ “የቻይና የኮቪድ-19 እርምጃዎች ምርጡ፣ ወጪ ቆጣቢ ነው ስለዚህም በተሻለ መልኩ ይቀጥላል” ማለታቸው አይዘነጋም፡፡
ሱን ዬሊ ይህን ይበሉ እንጅ ቻይና በጀመረችው የዜሮ-ኮቪድ ፖሊሲዋ ከቀጠለች ከተቀረው ዓለም የተገለለች እንዳያደርጋትና ሌላ ችግር እንዳያስከትከል በርካቶች የሚያነሱት ስጋት ነው፡፡
በተያያዘ የ“ዜሮ-ኮቪድ ፖሊሲ” የጋብቻ እና የወሊድ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ አስተዋጽኦ እንዳደረገ የቻይና ብሄራዊ ጤና ኮሚሽን በቅርቡ አስታውቋል፡፡
ኮሚሽኑ “ኮሮና ቫይረስ በአንዳንድ ሰዎች ጋብቻ እና ልጅ መውለድ ላይ ግልጽ ተጽዕኖ አሳድሯል” ብሏል።