ፑቲን ሰሜን ኮሪያን እንዲጎበኙ በኪም የቀረበላቸውን ጥሪ መቀበላቸውን ክሬሚሊን አስታወቀ
የሰሜን ኮሪያ እና ሩሲያ መቀራረብ በዩክሬን ያለው ጦርነት እንዲጠነክር እና ኪም ወሳኝ የሆነ የሚሳይል ቴክኖሎጂ እንዲያገኙ ያደርጋል የምትለውን አሜሪካ ስጋት ውስጥ ገብታለች
የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ፑቲቭ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በጥቅምት ወር ወደ ፒዮንያንግ እንደሚጓዙ ተናግረዋል
ፕሬዝደንት ፑቲን ሰሜን ኮሪያን እንዲጎበኙ በሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን የቀረበላቸውን ጥሪ "በደስታ" መቀበላቸውን ክሬሚሊን አስታውቋል።
የሰሜን ኮሪያ እና ሩሲያ መቀራረብ በዩክሬን ያለው ጦርነት እንዲጠነክር እና ኪም ወሳኝ የሆነ የሚሳይል ቴክኖሎጂ እንዲያገኙ ያደርጋል የምትለው አሜሪካ ስጋት ውስጥ ገብታለች።
ግብዣው የተደረገው ሁለቱ መሪዎች በምስራቅ ሩሲያ በወታደራዊ ፣ በዩክሬን ጦርነት እና የሰሜን ኮሪያን ሳተላይት ፕሮግራም በመደገፍ ጉዳዮች ባደረጉት ስብሰባ ላይ ነው።
ፑቲን ሩሲያን ለጎበኙት ኪም ዘመናዊ የተባለውን የስፔስ ማምጠቂያ ጣቢያ አሳይተዋቸዋል፤ ከመከላከያ ሚኒስትሮቻቸው ጋር በመሆንም ውይይት አካሂደዋል።
የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ፑቲን ግብዣውን በደስታ እንደተቀቡለት እና የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በጥቅምት ወር ወደ ፒዮንያንግ እንደሚጓዙ ተናግረዋል።
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ፕሬዝደንት ፑቲን ያደረጓቸው የውጭ ጉዞዎች ጥቂት ናቸው።
አሜሪካ እና አጋሮቿ እየተጠናከረ ያለው የሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ ግንኙነት አሳሳቢ ሆኖባታል።
አሜሪካ፣ ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ የጦር መሳሪያ እያቀረበች ነው የሚል ክስ እያቀረበች ነው። ነገርግን እስካሁን ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ መሳሪያ መስጠቷ ወይም አለመስጠቷ ግልጽ አይደለም።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌ ሾይጉ ባለፈው ሀምሌ ወር ሰሜን ኮሪያን በጎበኙበት ወቅት ጥቅም ላይ እንዳይውል የተከለከል ሚሳይል ጎብኝተዋል።
ወታደራዊ ትብብራቸውን እንደሚያጠናክሩ የሚገልጹት ሰሜን ኮሪያ እና ሩሲያ የአሜሪካን ክስ አስተባብለዋል።የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ፑቲን ግብዣውን በደስታ እንደተቀቡለት እና የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በጥቅምት ወር ወደ ፒዮንያንግ እንደሚጓዙ ተናግረዋል