ፕሬዝደንት ፑቲን ፓትርያርክ ክሪል በመሩት የትንሳኤ የጸሎት መርሃግብር ላይ ተገኙ
ቤተክርስቲያኗ ሩሲያ በዩክሬን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት የሚቃወሙ ቀሳውስትን አባራለች የሚል ወቀሳ ሲቀርብባት ነበር
ፕሬዝደንት ፑቲን በሞሶኮ በሚገኘው በትልቁ የመድኃኔአለም ካቴድራል ውስጥ ቀይ ሻማ ሲያበሩ በጸሎት መርሃግብሩ ቪዲዮ ታይተዋል
ፕሬዝደንት ፑቲን ፓትርያርክ ክሪል በመሩት የትንሳኤ የጸሎት መርሃግብር ላይ ተገኙ።
ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እና ሌሎች በርካታ አማኞች የፑቲን ዋነኛ ደጋፊ ናቸው የሚባሉት የሩሲያ ኦርቶዶክ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ክሪል በመሩት የዛሬው የትንሳኤ የጸሎት መርሃግብር ላይ ተገኝተዋል።
ፕሬዝደንት ፑተን ከሞስኮ ከንቲባ ሰሬጌ ሶቢያኒን ጋር ሆነው በሞሶኮ በሚገኘው በትልቁ የመድኃኔአለም ካቴድራል ውስጥ ቀይ ሻማ ሲያበሩ በጸሎት መርሃግብሩ ቪዲዮ ታይተዋል።
- በስቀለት ማግስት የሚውለው ቅዳሜ /ቀዳም / ስያሜዎች…
- በዓለ ትንሣኤውን ለእግዚአብሔር ክብርና ለሰው ልጆች ደኅንነት በአንድነት በመቆም ልናሳልፈው ይገባል- አቡነ ማቲያስ
ፑቲን ቅዳሜ ምሽት ተጀምሮ እስከ እሁድ ረፋድ ድረስ በቀጠለው የጸሎት መርሃግብር በርካታ ጊዜ አማትቀዋል። ፓትርያርክ ክሪል "እየሱስ ተነስቷል" ብለው ሲያሳውቁ፣ ፑቲን እና ሌሎች አማኞች "አዎ፤ ተነስቷል" ሲሉ መልሰዋል። ፑቲን ከዚህ ሌላ አልተናገሩም።
ፓትርያርክ ክሪል አሁን ሶስተኛ አመት የያዘውን የዩክሬን ጦርነት በጥብቅ እንደሚደግፉ ይነገራል።ፕሬዝደንት ፑቲን በፈረንጆቹ የካቲት 2022 በትንሿ ጎረቤታቸው ላይ ልዩ ያሉትን ወታደራዊ ዘመቻ ከከፈቱ በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ሚሊዮኖች ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።
ፖትሪያርኩ የሩሲያ ቅዱስ ድንበር እንዲጠበቅ እና በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል ያለው አውዳሚ የሆነው ጦርነት እንዲቆም ጸልየዋል።
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ጨምሮ የኦርቶዶክስ አማኞች የትንሳኤ በዓልን በጁሊያን የቀን አቆጣጠር መሰረት በዛሬው እለት ሲያከብሩ አብዛኞቹ የምዕራብ ቤተክርስቲያናት ይህን ትልቅ በዓል ባለፈው ሳምንት አክብረውታል።
ፑቲን በትላልቅ የቤተክርስቲያኗ በዓላት ላይ ሁሌም ይገኛሉ። በገና በዓል ከሞስኮ ከተማ ውጭ በመንቀሳቀስ በመንፈሳዊ አገልግሎት ይሳፋሉ።
በፋሲካ እለት ፑቲን ከሶቬት ህብረት መውደቅ በኋላ በተገነባው የመንግስት እና የቤተክርስቲያኗን ግንኙነት ማሳያ ተደርጎ በሚወሰደው በወርቅ የተለበጠ ጉልላት ወደአለው መድኃኔአለም ቤተክርስቲያን ይሄዳሉ።
ቤተክርስቲያኗ ሩሲያ በዩክሬን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት የሚቃወሙ ቀሳውስትን አባራለች የሚል ወቀሳ ሲቀርብባት ነበር።