የሩሲያው ፖለቲከኛ ናቫልኒይ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈጸመ
የ47ቱ አመቱ ናቫልኒይ ከሞስኮ 1900 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የአርክቲክ እስር ቤት ውስጥ ነበር ህይወቱ ያለፈው
የፕሬዝደንት ፑቲን ዋነኛ ተቀናቃኝ የነበረው ሩሲያዊ ፖለቲካኛ አሌክሲ ናቫልኒይ የቀብር ሰነ ሰርአቱ በሞስኮ ዛሬ አርብ ተፈጽሟል
የሩሲያው ፖለቲከኛ ናቫልኒይ የቀብር ሰነ ስርዓት ተፈጸመ።
የፕሬዝደንት ፑቲን ዋነኛ ተቀናቃኝ የነበረው ሩሲያዊ ፖለቲካኛ አሌክሲ ናቫልኒይ የቀብር ሰነ ሰርአቱ በሞስኮ ዛሬ አርብ ተፈጽሟል።
በቀብር ስነ ስርዓቱ ወቅት የተገኙት በሺዎች የሚቆጠሩ ሩሲያውያን ስሙን ከፍ አድርገው መጥራታቸውን እና ለሞቱ ምክንያት ናቸው ያሏቸውን ባለስልጣናት ይቅር እንደማይሏቸው መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ከቦሪሶቪስኪዮ መካና መቃብር በተላለፈ ቪዲዮ ላይ የናቫልኒይ አባት አናቶሊ እና እናት ልዩድሚላ ለመጨረሻ ጊዜ አስከሬኑን ስመው ለመሰናበት ቆመው ታይተዋል።
የ47ቱ አመቱ ናቫልኒይ ከሞስኮ 1900 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የአርክቲክ እስር ቤት ውስጥ ነበር ህይወቱ ያለፈው።
የሩሲያ ባለስልጣናት ናቫልኒይ በእስር ቤቱ ውስጥ እንቅስቃሴ ካደረገ በኋላ ወዲያውኑ ራሱን ስቶ ህይወቱ ማለፉን ከሁለት ሳምንታት በፊት ይፋ አድርገው ነበር።
የናቫልኒይ ደጋፊዎች፣ ናቫልኒይ ተገድሏል የሚል ክስ አቅርበዋል።
ክሬሚሊን በናቫልኒይ ሞት ላይ የመንግስት ተሳትፎ የለበትም ሲል ክሱን አስተባብሏል።
የሩሲያ ባለስልጣናት የናቫልኒይን እንቅስቃሴ አክራሪ ሲሉ የፈረጁት ሲሆን ደጋፊዎቹንም በአሜሪካ የሚደገፉ ችግር ፈጣሪዎች ይሏቸዋል።
አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያን ሀገራት ለፕሬዝደንት ፑቲን ዋነኛ ተቀናቃኝ ለሆነው ናቫለኒይ ሞት ፑቲንን ተጠያቂ ማድረጋቸው ይታወሳል።