ፑቲን ለጎርቫቼቭ ብሄራዊ የቀብር ስነ ስርአት ነፈጉ፤ በቀብራቸውም ላይ አይገኙም
የመጨረሻው የሶቬት መሪ ጎርቫቼቭ ሶቬት ህብረትን ከመፈራረስ ማዳን ያልቻሉ መሪ ናቸው

ምእራባውያን ጎርቫቼቭ በሶቬት ኮሚኒስት ስር የነበረውን የምእራብ አውሮፓ ክፍል ከህብረቱ እንዲወጣ በማድረጋቸው ያወድሷቸዋል
የሩሲያ ፕሬዝደንት ፑቲን በሶቬት ህብረት የመጨረሻው መሪ ጎርቫቼቭ የቀብር ስነ ስርአት ላይ አይገኙም፡፡
በሩሲያ ቤተ መንግስት ክሬሚሊን ፊት ለፊት የሚገኘው ትልቅ አዳራሽ የቀድሞ የሶቬት መሩ የሆኑትን የቭላድሚር ሌኒን፣ ጆሴፍ ስታሊን እና ሎንድ ብሬንዚኔቨን የቀብር ስነ ስርአት አስተናግዷል፡፡
የጎርቫቼቭ የቀብር ስነ ስርአት በወደታደር የሚታጀብ ቢሆንም ብሄራ የቀብር ስነ ስርአር ግን እንደማይካሄድላቸው ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ጎርቫቼቭ በ91 አመታቸው ነው ህይወታቸው ያለፈው፡፡
ፕሬዝደንት ፑቱንም በጎርቫቼቭ የቀብር ስነ ስርአት አይገኑም፡፡ የመጨረሻው የሶቬት ህብረት መሪ የነበሩት እና ሶቬት ህብረትን ከመፈራረስ መታደግ ያልቻሉት ጎርቫቼቭ ለብሄራዊ ቀብር ስነ ስርአት አልታደሉም፡፡
ምእራባውያን ጎርቫቼቭ በሶቬት ኮሚኒስት ስር የነበሩትን የምእራብ አውሮፓ ክፍል ከህብረቱ እንዲወጣ በማድረጋቸው ያወድሷቸዋል፡፡
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ሌየን በጎርባቼቭ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸው ፤"የነጻ አውሮፓን መንገድ የጠረገ ታማኝ መሪ" ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ባጋሩት ጽሁፍ የቀድሞ የሶቭየት መሪን ገልጸዋቸዋል።
ፕሬዝደንት ፑቲን ጎርቫቼቭ ህይወታቸው ባለፈበት ሆስፒታል የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡