ፑቲን ከዋግነር ከፍተኛ ኃላፊ ጋር በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ መከሩ
ፑቲን የዋግነር ተዋጊዎችን በዩክሬን ጦርነት እንዴት መጠቀም ይቻላል በሚለው ጉዳይ ነው ከኃላፊው ጋር የመከሩት
ፑቲን ዋግነር አመጽ ከፈጸመ ከወራት በኋላ በአንድሬ ትሮሼቭ መሪነት ለሩሲያ መዋጋት የሚችልበት እድል መኖሩን ገልጸው ነበር
ፑቲን ከዋግነር ከፍተኛ ኃላፊ ትሮሼቭ ጋር በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ መምከራቸው ተገለጸ።
ፑቲን የዋግነር ተዋጊዎችን በዩክሬን ጦርነት እንዴት መጠቀም ይቻላል በሚለው ጉዳይ ነው ከኃላፊው ጋር የመከሩት።
ውይይቱ ባለፈው ነሐሴ ወር በአውሮፕላን አደጋ የሞተው የዋግነር መሪ ፕሪጎዥን በሞስኮ ላይ አመጽ ከፈጸመ በኋላ የተደረገው ሞስኮ ቡድኑ በራሷ ስር እንደሆነ ለማሳየት መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ፑቲን ዋግነር አመጽ ከፈጸመ ከወራት በኋላ በአንድሬ ትሮሼቭ መሪነት ለሩሲያ መዋጋት የሚችልበት እድል መኖሩን ገልጸው ነበር።
በቅጽል ስሙ ሰዲዮ የሚባሉት ትሮሼቭ ከፕሬዝደንት ፑቲን እና ከምክትል መከላከያ ሚኒስትር ዩኑስቤክ የቭኩሮቭ ጋር ቁጭ ብለው ሲወያዩ ታይተዋል።
ፑቲን ለትሮሼቭ እንደተናገሩት የዋግነር ቡድን ሩሲያ በዩክሬን እያደረገች ባለችው ወታደራዊ ዘመቻ መሳተፍ ይችላሉ ብለዋል።
" ከአመት በላይ ተዋግታችኋል። ምን እንደሆነ እና እንዴት እንደሚካሄድ ታውቁታላችሁ" ሲሉ ፑቲን ተናግረዋል።
ፕሬዝደንቱ አክለውም በውጊያው ለሚሳተፉ የተለየ ድጋፍ እንደሚደርጉም ገልጸዋል።
የዋግነር ቡድን ከሩሲያ መከላከያ ሰራዊት ጋር በመወገን በዩክሬን ውስጥ ባክሙት እና በተለያዩ ግንባሮች ድል አስመዝግበው ነበር።
ዋግነር ከዩክሬን መልስ በሩሲያ መንግስት ላይ አምጾ ነበር። በጎረቤት ቤላሩስ አደራዳሪት ዋግነር አመጹን አቁሞ ወደ ቤላሩስ እንዲኮበልል ስምምነት መደረሱ ይታወሳል።