ፖለቲካ
ከዋግነር ጋር ስማቸው የተነሳው ጄነራል በወታደራዊ ልኡክ ውስጥ መካተታቸው ወደ ስራ መመለሳቸውን ግልጽ የሚያደርግ ነው ተባለ
ጄነራል ሰርጌ ሱርቪኪን አልጀሪያ የመከላከያ መለያቸውን ሳይለብሱ ታይተዋል
ጄነራሉ ስለ ዋግነር አመጹ አስቀድመው ያውቁ ነበር ተብሏል
ከሸፈ ከተባለው የዋግነት 'ክህደት' ጋር ስማቸው ሲነሳ የነበረው የሩሲያ ጄነራል ሰርጌ ሱርቪኪን ከሀገሪቱ የወታደራዊ ልዑክ ጋር አልጀሪያ ገብተዋል።
ጄነራሉ ከቅጥረኛ ቡድኑ የሰኔ ወር አመጽ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው የነበረ ሲሆን፤ አሁን ግን ለይፋዊ ኃላፊነታቸው መመለሳቸው ተነግሯል።
የሩሲያ መሳሪያ ከፍተኛ ገዢ በሆነችው አልጀሪያ የመከላከያ መለያ ሳይለብሱ ታይተዋል።
በሶሪያ ጦርነት ባሳዩት ብቃት ስማቸውን የገነቡት ጄነራል ሰርጌ ሱርቪኪን፤ በጥር ወር ከኃላፊነታቸው እስኪነሱ ድረስ የዩክሬን ጦር ዘመቻን መርተዋል።
በጥር ወር ዋግነር አምጾ ወደ ሞስኮ ሲገሰግስ ከቡድኑ ጋር ባላቸው ግንኙነት አይን ውስጥ ገብተዋል።
በቅርቡ በአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸው ባለፈው የዋግነር አዛዦ ፕሪጎዚ ሲወደሱም ነበር።
ጄነራል ሰርጌ ሱርቪኪን ከዋግነር አመጽ በኋላ ከህዝብ አይን ተሰውረዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ኒዮርክ ታይምስ የአሜሪካ የደህንነት ሹማምንትን ጠቅሶ ጄነራሉ ስለ አመጹ አስቀድመው ያውቁ ነበር ተብሏል።
በርካታ መገናኛ ብዙኸን ጄነራል ሰርጌ ከክሬምሊን ጋር መጎረባበጣቸውን ሲዘግቡ ቆይተዋል።