በአመጹ ወቅት የዋግነር ተዋጊዎች ወደ ሩሲያ ኑክሌር ሰፈር ተቃርበው ነበር ተባለ
የዩክሬን የወታደራዊ ደህንነት ኃላፊ ኪይርይሎ ቡዳኖቭ እንደተናገሩት የዋግነር ታጣቂዎች ርቀው ሄደው ነበር ብለዋል
የዋግነር መሪ ፕሪጎዥንም በድርድሩ መሰረት ወደ ቤላሩስ እንዲሄድ ስምምነት ላይ መደረሱ ይታወሳል
የሩሲያ ዋግነር ቡድን አመጽ ባከሄደበት ወቅት ተዋጊዎቹ ወደ ሩሲያ የኑክሌር ሰፈር ተቃርበው ነበር ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ባለፈው ሰኔ 24 አመጸኞቹ የዋግነር ኃይሎቾ ወደ ሞስኮ በሚገሰግሱበት ወቅት ተጠባባቂ የነበረ ወታደራዊ ተሽከርካሪ ጠንካራ ጥበቃ ወደሚደረግበት የኑክሌር ጦር መሳሪያ ወደያዘው ሰፈር በምስራቅ አቅጣጫ መንቀሳቀሱን የአካባቢዎ ነዎሪዎች እና በማህበራዊ ሚዲያ የወጣ ቪዲዮ ያሳያል።
ነገርግን የዩክሬን የወታደራዊ ደህንነት ኃላፊ ኪይርይሎ ቡዳኖቭ እንደተናገሩት የዋግነር ታጣቂዎች ርቀው ሄደው ነበር ብለዋል።
ኃላፊው እንዳሉት ተዋጊዎቹ ኑክሌር ሰፈሩ መድረሳቸውን እና የኑክሌር መሳሪያ ለማግኘት ነበር ብሏል።"ምክንያቱም አንድ ሰው እስኪቀር ለመዋጋት ከወሰንክ አቅምህን የሚያሳድገው ያ ነው" ሲሉ ቡዳኖቭ ተናግረዋል።
ሮይተርስ የዋግነር ታጣቂዎች ቮሮኔዝ-45 ስለመድረሳቸው ማረጋገጥ እንደማይችል ገልጿል።
ቡዳኖቭ ስጉዳዩ መከሰት መረጃ ማቅረብ አልቻሉም፤ ስለጉዳዩ ከአሜሪካ እና ሌሎቹ አጋሮቹ ጋር ስለመነጋገራየውም መልስ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆኑም።
ቡዳኖቭ አመጹ ለምን በአጭሩ እንደተቀጨም አልተናገሩም።
ነገርግን ጉዳዩን የሚያውቁ ሩሲያ በተቆጣጠረችው ምስራቅ ዩክሬን የሚኖር ምንጭ እንደናገረው ጉዳዩ ክሬሚሊንን አሳስቦ እንደነበረ እና አፋጣኝ ድርድር እንዲዲካሄድ ያደረገ ነው።
የቤላሩስ ፕሬዝደንት ሉካሸንኮ ባደረጉት ጥረት ዋግነር አመጹን እንዲያቆም እና ሩሲያም የመሰረተችበት የሀገር ክህደት ክስ እንዲነሳ ተደርጓል።
የዋግነር መሪ ፕሪጎዥንም በድርድሩ መሰረት ወደ ቤላሩስ እንዲሄድ ስምምነት ላይ መደረሱ ይታወሳል።