የሩሲያ መረጃ መንታፊዎች በዩክሬን የኤምባሲ ሰራተኞችን በርካሽ መኪና ማስታወቂያ መረጃ ለመበርበር ሞክረዋል ተባለ
ጠላፊዎቹ በኪየቭ ለሚሰሩ በደርዘን ለሚቆጠሩ የውጭ ዲፕሎማቶች ሀሰተኛ በራሪ ወረቀት ልከዋል ተብሏል
መረጃ መንታፊዎቹ ቢያንስ 22 ዲፕሎማቶች ላይ ያነጣጠረ ነው መሆኑ ተነግሯል
በደርዘን የሚቆጠሩ በዩክሬን የሚገኙ ዲፕሎማቶችን በውሸት የመኪና ማስታወቂያ ኢላማ አድርገዋል።
የስለላ ተግባሩ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ከሚገኙት ከ80 የሚጠጉ የውጭ ተልዕኮዎች ውስጥ ቢያንስ 22 ዲፕሎማቶችን ያነጣጠረ ነው ተብሏል።
በፓሎ አልቶ ኔትወርክስ ዩኒት 42 የተባለ የሳይበር ደህንነት ተንታኞች "ዘመቻው ጉዳት በሌለው እና ህጋዊ በሆነ ክስተት ነው የተጀመረው" ብለዋል።
በሚያዚያ 2023 አጋማሽ ላይ በፖላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ ያለ አንድ ዲፕሎማት ያገለገለ ቢ.ኤም.ደብሊው ተሽከርካሪዎችን ለመሸጥ ለኤምባሲዎች በኢሜል ልኳል ብለዋል።
የደህንነት ጉዳዮችን በመጥቀስ ማንነታቸውን ለመግለጽ ያልፈለጉት ፖላንዳዊ ዲፕሎማት በዲጂታል መረጃ ወረራው ውስጥ የማስታወቂያውን ሚና አረጋግጠዋል።
የደህንነት ተቋሙ ኤፒቲ 29 ወይም "ኮዚ ቤር" በመባል የሚታወቁት ጠላፊዎቹ፤ በራሪ ወረቀት መንታፊ አዘል ሶፍትዌሮች አድርገው በኪየቭ ለሚሰሩ በደርዘን ለሚቆጠሩ የውጭ ዲፕሎማቶች ልከዋል ብሏል።
በፈረንጆቹ 2021 የአሜሪካ እና የእንግሊዝ የስለላ ኤጀንሲዎች ኤፒቲ 29ን እንደ የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት ኤስ.ቪ.አር አካል አድርገው ለይተዋል።
የዩኒት 42 "ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮዎች ከፍተኛ ዋጋ ያለው የስለላ ኢላማ ይሆናሉ" ብሏል።
"ሩሲያ ዩክሬንን ጦርነት በጀመረች በ16ተኛው ወር በዩክሬን ዙሪያ ያለው መረጃ እና ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮዎች ለሩሲያ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች ናቸው" በማለት አክሏል።