ፑቲን በቤላሩስ ላይ የሚቃጣ ጥቃት በሩሲያ ላይ እንደተቃጣ ይቆጠራል አሉ
በሩሲያ ጎረቤት እና አጋር ላይ የሚሰነዘር ማንኛውም ጥቃት በሩሲያ እንደተቃጣ ጥቃት ይወሰዳል ብለዋል ፑቲን
የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማትሱዝ ሞራዊኪ በትዊተር ገጻቸው "ስታሊን የጦር ወንጀለኛ እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የፖላንድ ዜጎችን ህይወት ያጠፋ ነው" ብለዋል
ፕሬዝደንት ፑቲን በቤላሩስ ላይ የሚቃጣ ጥቃት በሩሲያ ላይ እንደተቃጣ ይቆጠራል ሲሉ ለፖላንድ ተናግረዋል።
ፕሬዝደንት ፑቲን በትናንትናው እለት እንደተናገሩት የኔቶ አባል የሆነችው ፖላንድ በቀድሞው የሶቬት ህብረት ውስጥ ግዛት የማስፋፋት እቅድ አላት የሚል ክስ አሰምተዋል።
በሩሲያ ጎረቤት እና አጋር ላይ የሚሰነዘር ማንኛውም ጥቃት በሩሲያ ላይ እንደተቃጣ ጥቃት ይወሰዳል ብለዋል ፑቲን።
ፑቲን በቴሌቪዝን በተላለፈ መልዕክታቸው በቤላሩስ ላይ ጥቃት የሚሰነዘር ከሆነ ሩሲያ አጸፋዊ ምላሽ ትሰጣለች ሲሉ ተናግረዋል።
የሞስኮ የጸጥታ ኮሜቴ የሩሲያ ቅጥረኛ ተዋጊ ዋግነር ግሩፕ ቤላሩስ ከገባ በኋላ ወደ ምስራቅ ፖላንድ እንዲንቀሳቀስ ማድረጓም ተዘግቧል። ፖላንድ በቤላሩስ ውስጥ ግዛት የመያዝ ፍላጎት አላት የሚለውን ክስ አስተባብላለች።
ፕሬዝደንቱ በመልእክታቸው ምዕራብ ፖላንድ በሶቬት መሪው ጆሴፍ ስታሊን ለሀገሪቱ የተሰጠ ነው ብለዋል።
ጉዳዩን በሚመለከት የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማትሱዝ ሞራዊኪ በትዊተር ገጻቸው "ስታሊን የጦር ወንጀለኛ እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የፖላንድ ዜጎችን ህይወት ያጠፋ ነው። ታሪካዊ እውነታው አያከራክርም" ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስሩ የሩሲያ አምባሳደር በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ይጠራሉም ብለዋል።
ቤላሩስ ወደ ሩሲያ የተዛወረው የሩሲያው ቅጥረኛ ታጣቂ ዋግነር ግሩኘ ከፖላንድ ድንበር በቅርብ ርቀት ላይ ለቤላሩስ ልዩ ኃይል ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ማስታወቋ ይታወሳል።