ፕሬዝደንቱ እንደገለጹት ሩሲያ ክለስተር ቦንብ የምትጠቀመው በሩሲያ ላይ የክለስተር ቦንብ ጥቃት ሲሰነዘር ነው ብለዋል
ፕሬዝደንት ፑቲን ሩሲያ "በቂ የክላስተር ቦንብ ክምችት" እንዳላት እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ልትጠቀምበት እንደምትችል ተናግረዋል።
ፕሬዝደንቱ እንደገለጹት ሩሲያ ክለስተር ቦንብ የምትጠቀመው በሩሲያ ላይ የክለስተር ቦንብ ጥቃት ሲሰነዘር ነው ብለዋል።
በቅርቡ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር በምታደርገው ጦርነት እጠቀመዋለሁ ያለችውን ክለስተር ቦንብ ከአሜሪካ መቀበሏን መግለጿ ይታወሳል።
ክለስተር ቦንብ ከፈነዳ በኋላ በውስጡ ያሉት ብዛት ያላቸው ትናንሽ ቦንቦች ተስፈንጥረው ሰፊ ቦታ የሚሸፍን ፍንዳታ ያስከትላሉ።
ሩሲያ የአሜሪካን ለዩክሬን ክለስር ቦንብ መለገስ ተቃውማዋለች።
"በርግጥ በኛ ላይ ጥቃት የሚሰነዝሩ ከሆነ፣ አጸፋዊ ምላሽ የመስጠት መብት አለን" ሲሉ ፑቲን ለሩሲያ ሚዲያዎች ተናግረዋል።
ዩክሬን የተቀበለችው መሳሪያ ጥቅም ላይ እንዳይዉል ከታገደ 100 አልፎታል።
ዩክሬን መሳሪያውን የምትጠቀምው የጠላት ኃይል ክምችት ባለበት ቦታ ላይ ብቻ ነው ብላለች።