ፕሬዝዳንት ፑቲን በደቡብ አፍሪካው የብሪክስ ጉባኤ ላይ እንደማይሳተፉ ተገለጸ
ደቡብ አፍሪካ የፊታችን ነሀሴ የብሪክስ ሀገራት መሪዎች ጉባኤን ታስተናግዳለች
ሩሲያ በዚህ ጉባኤ ላይ በውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ሰርጌ ላቭሮቭ ትወከላለች ተብሏል
ደቡብ አፍሪካ የፊታችን ነሀሴ የብሪክስ ሀገራት መሪዎች ጉባኤን ታስተናግዳለች።
በዚህ ጉባኤ ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጾ የነበረው የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እንደማይገኙ ስፑትኒክ ዘግቧል።
እንደዘገባው ከሆነ ሩሲያ በዚህ ጉባኤ ላይ በውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ሰርጌ ላቭሮቭ ትወከላለች ተብሏል።
ደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ወይም አይሲሲ ፈራሚ ሀገር መሆኗን ተከትሎ የእስር ማዘዣ የወጣባቸው ፕሬዝዳንት ፑቲን ወደ ግዛቷ ከመጡ አስራ የማስረከብ ግዴታ አለባት።
የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ " ፕሬዝዳንት ፑቲንን ማሰራ በሩሲያ ላይ ጦርነት እንደማወጅ ይቆጠራል" ሲሉ ከሰሞኑ ተናግረዋል።
በሩሲያ፣ ቻይና፣ ህንድ፣ ብራዚል እና ደቡብ አፍሪካ አማካኝነት የተመሰረተው ብሪክስ የተሰኘው ጥምረት በምዕራባውያን የበላይነት ይመራል ያለውን የዓለም ስርአት ለመቀየር አልሟል።
ብሪክስ የራሱ የሆነ የመገበበያ ገንዘብ ለማስተዋወቅ እየሰራ ሲሆን የዲዶላራይዜሽን ወይም ዶላርን ከመገበያያነት የማስወጣት ዘመቻን ይደግፋል።
ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ብሪክስን ለመቀላቀል ማመልከቻ አስገብተዋል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን በቀጣይ ወር በጆሃንስበርግ በሚካሄደው የብሪክስ (ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ) ጉባኤ መታደም እንደሚፈልጉ ተገልጿል።