ፑቲን ሩሲያ በውጊያው አዲስ ሚሳይል መሞከሯን እንደምትቀጥል ተናገሩ
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ኪቭ አዳዲስ አደጋዎችን ለመከለል ከምዕራባውያን አጋሮቿ ጋር እየሰራች ነው ብለዋል

ዩክሬን ሚሳይሉ በሰአት 13ሺ ኪሎሜትር እንደሚጓዝ እና ኢላማ ለመምታት 15 ደቂቃ እንደማፈጅበት ገልጻለች
ፑቲን ሩሲያ በውጊያው አዲስ እንደምትቀጥል መሞከሯን እንደ ተናገሩ።
የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ሩሲያ የኦሬሽንክ ሚሳይል ክምችት እንዳላት እና በውጊያ መጠቀሟን እንደምትቀጥል ሲገልጹ ዘለንስኪ ደግሞ ይህን መሳሪያ የለማክሸፍ የሚያስችል የአየር ሲስተም እያለማች መሆኑን ገልጸዋል።
ፑቲን የመካከለኛ ርቀት ሚሳይል ባስወነጨፈች ማግስት ባሰሙት ንግግር ሩሲያ ኦሬሽንክ የተባለውን አዲስ ሚሳይል ያስወነጨፈችው ዩክሬን የአሜሪካ ባለስቲክ ሚሳይልን እና የእንግዝን ክሩዝ ሚሳይል ወደ ሩሲያ በማስወንጨፏ ምክንያት ነው።
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ኪቭ አዳዲስ አደጋዎችን ለመከለል ከምዕራባውያን አጋሮቿ ጋር እየሰራች ነው ብለዋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው ኦሬሽንክ ሚሳይል ስኬታማ መሆኑን የገለጹት ፑቲን ተጨማሪ ሙከራዎች እንደሚደረግ ተናግረዋል።
"ሁኔታውን እና የደህንነት ስጋቱን እያየን እነዚህን ሚሳይሎች መሞከራችንን እንቀጥላለን" ሲሉ ፑቲን በቴሌቪዥን በተላለፈው መግለጫቸው ተደምጠዋል።"የእነዚህ አይነት መሳሪያዎች ክምችት አለን።"
የአሜሪካ ባለስልጣናት ግን ሩሲያ የተጠቀመችው ሚሳይል ለሙከራ ብቻ ነው፤ ያላት ክምችትም የተወሰነ ነው ብለዋል። ኢንተርሚዲየት ሚሳይል ከ3000-3500 ኪሎሜትር ርቀት መምዘግዘግ የሚችል ሲሆን የትኛውንም የአውሮፓ ወይም የአሜሪካ ቦታ መምታት ይችላሉ።
የደህንነት ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ ኦሬሽንክ ሚሳይል በአንድ ጊዜ ብዙ ቦታዎችን መምታት የሚችሉ በርካታ ተተኳሾችን መያዝ የሚችል መሆኑ የተለየ ያደርገዋል። ባለሙያዎቹ ከአህጉር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳይል ጋር የመመሳሰል ባህሪ አለው ብለዋል።
ዩክሬን ሚሳይሉ በሰአት 13ሺ ኪሎሜትር እንደሚጓዝ እና ኢላማ ለመምታት 15 ደቂቃ እንደማፈጅበት ገልጻለች።
ዩክሬን በምዕራባውያን ሚሳይሎች የሩሲያን ግዛት መምታቷ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ውጥረት ከፍተኛ ደረጃ እንዲደርስ አድርጎታል።
ሩሲያ ዩክሬን የምዕራባውያን ሚሳይሎችን በሩሲያ ግዛት ውስጥ ያሉ ኢላማዎችን እንድትመታ በመፍቀድ፣ አሜሪካ እና አጋሮቿ ከሩሲያ ጋር ወደ ቀጥተኛ ግጭት እየተገቡ ነው። ባለፈው ማክሰኞ ፑቲን ሩሲያ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ልትጠቀም የምትችልባቸውን መስፈርቶች ዝቅ የሚያደርገው ፖለሲ ተግባራዊ እንዲሆን ፊርማቸውን አኑረዋል።
አዲሱን የሩሲያ ሚሳይል ተኩስ ግጭት አባባሽ ሲሉ የገለጹት ዘለንስኪ መከላከያ ሚኒስትሩ እሳቸውን ወክለው ከምዕራባውያን አጋሮች በአየር መከላከያ ስርአት ዙሪያ እየተወያዩ ነው ብለዋል።ዩክሬን ሚሳይሉ በሰአት 13ሺ ኪሎሜትር እንደሚጓዝ እና ኢላማ ለመምታት 15 ደቂቃ እንደማፈጅበት ገልጻለች።