ፑቲን የሩሲያ ኑክሌር ኃይል 95 በመቶ መዘመኑን ገለጹ
ፑቲን የሩሲያ አየር ኃይል አራት ኑክሌር የመሸከም አቅም ያላቸው ሱፐርሶኒክ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖችን ማምረቱን በምሳሌነት ጠቅሰዋል
ሩሲያ እያመረተች ያለችውን ዘመናዊ መሳሪያዎች ተወዳዳሪ እንደሌላቸው በተደጋጋሚ እየገለጸች ነው
ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን የሩሲያ ኑክሌር ኃይል 95 በመቶ መዘመኑን ገለጹ።
የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን 95 በመቶ የሚሆነው የሩሲያ ስትራቴጂክ ኑክሌር ኃይል መዘመኑን ገልጸዋል።
ፑቲን የሩሲያ አየር ኃይል አራት ኑክሌር የመሸከም አቅም ያላቸው ሱፐርሶኒክ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖችን ማምረቱን በምሳሌነት ጠቅሰዋል።
ፕሬዝደንት ፑቲን ይህን ያሉት ቱ-160ኤም በተባለችው ኑክሌር ተሸካሚ ቦምብ ጣይ አውሮፕላን ላይ ሲበሩ ከታዩ ከአንድ ቀን በኋላ በተከበረው 'የአባት ሀገር ተከላካይ' አመታዊ ቀን ላይ ነው።
ፑቲን በዩክሬን የተጀመረው ጦርነት ሁለተኛ አመት ዋዜማ ላይ በዩክሬ "ለእውነት እና ለፍትህ" እየተዋጉ ነው ያሏቸውን ወታደሮች ጀግኖች ሲሉ አሞግሰዋቸዋል።
የሩሲያ የመሬት፣ የባህር እና የአየር የኑክሌር አቅም መዘመኑን እና በየጊዜው እየዘመነ እንዲሄድ እየተደረገ መሆኑን ፑቲን ተናግረዋል።
"በአሁኑ ወቅት ዘመናዊ መሳራያዎች በስትራቴጂክ ኑክሌር ኃይላችን ውስጥ 95 በመቶ ድርሻ ይዘዋል። የባህር ኃይል 'ኑክሌር ትሪያድ' ወይም ኑክሌር ኃይል ሙሉ በሙሉ ዘምኗል።"
ሩሲያ ፑቲን ግልጽ ያላረጉት የተኩስ ስርአት ያለውን አዲሱን ዚርኮን ሚሳይል ማሞረት ጀምራለች ብለዋል።
ፑቲን "ቀጣዩ ስራ አስተማማኝ የሆኑ ሞዴሎችን መስራት ማምረት እና በወታደራዊ ዘርፎች ሰውሰራሽ አስተውሎትን ማስተዋወቅ ነው"ሲሉም ተናግረዋል።
ሩሲያ እያመረተች ያለችውን ዘመናዊ መሳሪያዎች ተወዳዳሪ እንደሌላቸው በተደጋጋሚ እየገለጸች ነው።
በትናንትናው እለት ፑቲን ሲበሩባት የታየችው ቱ-160ኤም የተሰኘችው ኑክሌር ተሸካሚ ቦምብ ጣይ አውሮፕላን 12 ሚሳይሎችን ተሸክማ 12ሺ ኪሎሜትር መብረር እንደምትችል ተገልጿል።